ዋሽንግተን ዲሲ —
የማሊ ምርጥ የጥበብ ሰው /አርቲስት/ ማን ነው? ይህ ጥያቄ ዛሬውኑ በማሊው የሙዚቃ ፌስቲቫል ዝግጅት ላይ እየተናኘ ነው።
በዝርዝሩ ውስጥ ናሃዋ ዱምቢያን፤ ኡሙ ሳንጋሬን የአምናዎቹን ድንቅ ብልጭታዎች የቲምቡክቱ ልጆች የሚንጥ ባንድ ሳንጎይ ብሉዝ፤ እንዲሁም በድፍን ምዕራብ አፍሪካ የኮራ ንጉሥ ተብሎ የገነነው ሲድኪ ዲያባቴ፤ እንግሊዛዊው ዘፋኝ እና የዘፈን ደራሲ ዳመን አልባርንን ያካትታል።
ወታደሮች መፈንቅለ-መንግሥት ካደረጉና ጂሃዲስቶች የሃገሪቱን ሰሜን ከተቆጣጠሩ አራት ዓመት ከተቀጠሩ በኋላ ማሊ ዛሬ እያንሠራራች የምዕራብ አፍሪካ የጥበብና የባሕል መናገሻነቷን እንደገና ለማፅናት እየጣረች ነች። ለሙሉው ዘገባ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።