በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የራዲዮ መፅሔት ልዩ ልዩ ቅንብሮች! የኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክና ሙዚቀኞች


የሳምንቱ የእረፍት ጊዜ የእሁድ ምሽት የመዝናኛ ምርጫችሁ ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ።የራዲዮ መጽሄት ወጎች፥ በ“ወርቃማው ዘመን ትዝታዎች፤” የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ የፎቶ መጽሃፍ ህትመት፤ በሮክ ሙዚቃ አቀንቃኞቹ ጃኖ የሙዚቃ ቡድን አባላት የዓለም ዙሪያ የሙዚቃ ትዕይንት የዋሽንግተን ጉዞና እንዲሁም ቆይታ ከረቂቅ (ክላሲክ ሙዚቃ) ተጫዋች ጋር።

የውይይቶቹ ተሳታፊዎች፥ የፎቶ መጽሃፉ አዘጋጅ አቶ አብረሃም ብዙነህ፤ አርቲስት ታማኝ በየነና አንጋፋው ድምጻዊ መልካሙ ተበጀ፤ የጃኖ የሙዚቃ ባንድ መሪ ኪሩቤል ተሥፋዬና የባንዱ መሥራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ አዲስ ገሰሰ፤ እንዲሁም፤ ረቂቅ (ክላሲክ ሙዚቃ) ተጫዋቹ ግርማ ይፍራሸዋ ናቸው።
XS
SM
MD
LG