በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ምዕራብ ሊቢያ ውስጥ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ 50 ሰዎች ሞተዋል


በቦምቡ ምክንያት የቆሰለ ሰው በሊብያ ምስራታ ሆስፒታል እየታከመ [ፎቶ - ሮይተርስ/ REUTERS]
በቦምቡ ምክንያት የቆሰለ ሰው በሊብያ ምስራታ ሆስፒታል እየታከመ [ፎቶ - ሮይተርስ/ REUTERS]

ምዕራብ ሊቢያ ውስጥ ግዙፍ ፈንጂ የተጠመደበት መኪና በአንድ የፖሊሶች ማሰልጠኛ ማዕከል ላይ ባደረሰው ጥቃት፥ በትንሹ ለ50 ሰዎች መገደልና ለሌሎች በርካቶች መጎዳት ምክንያት ሆኗል።

በባለሥልጣናትና የሃገር ውስጥ ዜና ዘገባዎች መሠረት፥ ዛሬ ምዕራብ ሊቢያ ውስጥ ግዙፍ ፈንጅ የተጠመደበት መኪና በአንድ የፖሊሶች ማሰልጠኛ ማዕከል ላይ ባደረሰው ጥቃት፥ በትንሹ ለ50 ሰዎች መገደልና ለሌሎች በርካቶች መጎዳት ምክንያት ሆኗል።

ቦምቡ የፈነዳው ዚሊተን(Zliten) ከተማ ውስጥ በሚገኘው ማዕከል በመቶዎች የሚገመቱ ምልምሎች በተሰበሰቡበት ወቅት ነው።

በጥቃቱ የሞቱት ሰዎች 50 መሆናቸውን የዜና ዘገባዎች ቢገልጹም፥ የሆስፒታል ምንጮች ግን የሰለባዎቹን ቁጥር 65 ያደርሱታል።

ለጥቃቱ እስካሁን ኃላፊነቱን የወሰደ የለም።

በሊቢያ የተባበሩት መንግሥታት ተልዕኮ አስተባባሪ ማርቲን ኮብለር (Martin Kobler) በትዊተር (Twitter) መልዕክታቸው፥ ”ጥቃቱ በአጥፍቶ ጠፊ የተፈጸመ ነው” ሲሉ አውግዘው፥ ሊብያውያን ባስቸኳይ ተባብረው አሸባሪነትን እንዲዋጉ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ሊቢያ ባሁኑ ወቅት፥ ትሪፖሊ(Tripoli)ን በሚቆጣጠረው እስላማዊ አስተዳደርና ዓለምአቀፍ እውቅና ባገኘውና ወደ ምሥራቅ ቶብሩክ(Tobruk) በሸሸው ፓርላማ ተከፍላለች።

የዜና ዘገባ አለን የድምጽ ፋይሉን በመጫን ያዳምጡ።

ምዕራብ ሊቢያ ውስጥ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ 50 ሰዎች ሞተዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:10 0:00

XS
SM
MD
LG