በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሊብያ የኢትዮጵያዊያን ክርስቲያኖች ግድያ


ብርቱ ኀዘን
ብርቱ ኀዘን

የኢትዮጵያ ፓርላማ በነገ - ማክሰኞ ስብሰባው አይሲል በሚባለው የሽብር ቡድን ሊብያ ውስጥ ለተገደሉት ኢትዮጵያዊያን ብሔራዊ ኀዘን እንደሚያውጅ ተገለፀ፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:21:51 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የኢትዮጵያ ፓርላማ በነገ - ማክሰኞ ስብሰባው አይሲል በሚባለው የሽብር ቡድን ሊብያ ውስጥ ለተገደሉት ኢትዮጵያዊያን ብሔራዊ ኀዘን እንደሚያውጅ ተገለፀ፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ባን ኪ-ሙንም ግድያውን አውግዘው ከዳዪሽ ወይም አይሲል ጋር ግብርአበር በሆኑ ሰዎች የተፈፀመውን ግድያ አረመኔያዊ በማለት አውግዘዋል፡፡

ለተጎጂዎቹ ቤተሰቦችና ለኢትዮጵያ መንግሥትም የኀዘን መግለጫ ልከዋል፡፡

አይሲል የፈፀመው ግድያ ኢትዮጵያ ላይ ወይም ክርስትና ላይ ሳይሆን በሙሉ የሰው ዘር ላይ ነው ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ ተናግረዋል፡፡

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ አምባሣደር ዶ/ር ተቀዳ ዓለሙም አድራጎቱን አውግዘዋል፡፡

የአዲስ አበባ መጅሊስ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሕመድ አብዱልረሕማንም አድራጎቱን እሥላማዊ ያልሆነ ብለውታል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ዋሸንግተን ዲ.ሲ የሚገኘው ፈርስት ሂጅራ ፋውንዴሽን የሚባለው ድርጅት ባወጣው መግለጫ አድራጎቱን እጅግ የሚዘገንን፣ ሕሊናን የሚያስነውር የጭካኔ አድራጎት ነው ሲል ውግዘቱን አሰምቷል፡፡

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝም ማምሻውን በቴሌቪዥን ባሰሙት ንግግር ኢትዮጵያዊያን በዚህ ፈታኝ ወቅት አብረው እንዲቆሙ ጠይቀዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG