በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከስልሳ በላይ በሊቢያ የነበሩ ኢትዮጵያውያን፥ ኤርትራውያንና ሌሎች አፍሪቃውያን ስደተኞች ያለቁበትን አደጋ UNHCR ባወጣው መግለጫ አረጋገጠ።


ኤርትራውያንና ሶማሊያንውያንን ጨምሮ የሚበዙት ኢትዮጵያውያን የሆኑባቸው 72 ስደተኞች በብጥብጥ በመታመስ ላይ ካለችው ሊቢያ በጀልባ ወደ ጣልያን ወደብ በማቅናት ላይ ሳሉ 61 ያሉቁበትን ዜና መዘገባችን ይታወሳል።

በህይወት ተርፈው ከተነሱበት የሊቢያ ባህር ዳርቻ ለመመለስ ከበቁት አስራ አንዱ ሁለቱ መሞታቸው ተመልክቷል።

እንዲህ ያለ አሳዛኝ እልቂት እንዴት ሊደርስ ቻለ? አቅጣጫ ስተውና ነዳጅ አልቆባቸው በባህሩ ላይ ሲንገዋለሉ የተመለከቷተው የተለያዩ ወገኖችስ እንዴት ሳይታደጓቸው ቀሩ? የተረፉትም ሆነ ቀጣይ መሰል ዕጣ ከፊታቸው የተደቀነው ሌሎች ባሁኑ ሰዓት በምን ሁኔታ ላይ ይገኛሉ? የሚሉ ጥያቄዎችን ይዞ አሉላ ከበደ በህወት ለመትረፍ ከበቁት ዘጠኝ ኢትዮጵያውያን አንዱንና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ፅ/ቤት የቱኒዝያ ልዑክ ቃል አቀባይ Hlene Coux’ን ስደተኞቹ ከሚገኙበት ቱኒዝያ ድንበር ላይ ከሚገኘው Shousha ካምፕ በስልክ አነጋግረናል።

ለዘገባው ዝርዝር ተከታዩን ያዳምጡ

XS
SM
MD
LG