በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሎረን ባግቦ ባለቤት ሲሞን ባግቦ ዛሬ በአይቮሪስት ፍርድ ቤት ቀርበዋል


የቀድሞው የአይቮሪኮስት ፕረዚዳንት ሎረን ባግቦ እና ባለቤታቸው ሲሞን ባግቦ /ፋይል ፎቶ/
የቀድሞው የአይቮሪኮስት ፕረዚዳንት ሎረን ባግቦ እና ባለቤታቸው ሲሞን ባግቦ /ፋይል ፎቶ/

የቀድሞው የአይቮሪኮስት ፕረዚዳንት ሎረን ባግቦ እ.አ.አ. ከ 2010 እስከ 2011 ዓ.ም በነበረበት ጊዜ በስብእና ላይ ወንጀል ፈጽመዋል ተብለው በአለም አቀፍ የወንጀል ችሎት ፊት መቀረባቸው በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት ተመሳሳይ ክስ የተመሰረተባቸው ባለቤታቸው ሲሞን ባግቦ የፍርድ ሂደት ደግሞ ዛሬ በአይቮሪኮስት ተጀምሯል።

ሲሞን ባግቦ አቢጃን በሚገኘው የወንጀል ችሎት በገቡበት ወቅት ደጋፊዎቻቸው የሞቀ አቀባበል አድርገዋላቸዋል።

የቀድሞዋ ቀዳማዊት እመቤት እ.አ.አ. ከ 2010 እስከ 2011 ዓ.ም በነበረው ጊዜ ውስጥ በስብእና ላይ ወንጀል ፈጽመዋል ተብለው ለፍርድ የቀረቡት ያኔ በተካሄደው ፕረዚዳንታዊ ምርጫ ፕረዚዳንት የነበሩት ባለቤታቸው ሎረን ባግቦና የወቅቱ ፕረዚዳንት አላሳን ዋታራ አሸንፈናል ማለታቸው ግጭት ባስከተለበት ወቅት ተፈጸመ በተባለው ወንጀል ምክንያት ነው። በተከተለው ግጭት ቢያንስ 3,000 ሰዎች አልቀዋል።

ባለቤታቸው ባግቦ ሄግ በሚገኘው በአለም አቀፍ የወንጀል ችሎት በቀረቡበት በአሁኑ ወቅት ሲሞን ባግቦ በአይቮሪኮስት የሚዳኙት የሀገሪቱ ፍርድ ቤት በሳቸው ላይ የመበየን ብቃት አለው በማለት የሀገሪቱ ባለስልጣኖች ወደ አለም አቀፍ ችሎት አናስተላልፋቸውም በማለታቸው ነው።

ሮድሪግ ዳድጄ (Rodrigue Dadje) የተባሉት ጠበቃቸው ሚሲስ ባግቦ የተከሰሱት በዜጎቻቸው ላይ ወንጀል ፈጽመዋ በሚል ስለሆነ ህዝባቸው ፌት ቀርበው መልሳቸውን ለመስጣት እንዲችሉ በሃገራቸው መዳኘቱን ይምርጣሉ ብለዋል። ይሁንና የአይቮሪኮስት ፍርድ ቤት ከመንግስት ተፅዕኖ ነጻ ባለመሆኑ ማስረጃ ባይገኝባቸውም እንኳን ሊፈረድባቸው ይችላል ሲሉ አስገንዝበዋል።

66 አመት እድሜ የሆናቸው ሲሞን ባግቦ አንድ ሌላ ፍርድ ቤት የሃገር ጸጥታን አደጋ ላይ ጥለዋል። የታጠቁ ዱርየዎችንም አደራጅተዋል በሚል ባለፈው አመት የ 20 አመታት እስራት ፈርዶባቸው ነብር። እሳቸው ግን ጥፋተኛ አይደለሁም እንዳሉ ናቸው።

ሲሞን ባግቦ ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ እድሜ ይፍታሽ ሊፈረድባቸው ይችላል። ኤምሊ ዮብ ከአቢጃን ያጠናቀረችውን ዘገባ አዳነች ፍሰሀየ አቅርባዋለች ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።

የሎረን ባግቦ ባለቤት ሲሞን ባግቦ ዛሬ በአይቮሪስት ፍርድ ቤት ቀርበዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:22 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG