በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“በአይቮሪ ኮስት ላይ የተፈጸመው ጥቃት መወገዝ አለበት" - ጄ ፒተር ፋም


ታጣቂዎች በአይቮሪ ኮስት ግራንድ ባሳም መዝናኛ ስፍራ ላይ ዛሬ ጥቃት ፈጽመዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:33 0:00

ታጣቂዎች በአይቮሪ ኮስት ግራንድ ባሳም መዝናኛ ስፍራ ላይ ዛሬ ጥቃት ፈጽመዋል

“በአይቮሪ ኮስት ላይ የተፈጸመው ጥቃት መወገዝ አለበት። አል-ቃዒዳ በእስላማዊ መግረብና አጋሮቹ ሰላማዊ ሰዎችን በመፍጀት ተግባራቸው ምን ያህል ጨቃኞች እንደሆኑ ያሳያል"በዩናይትድ ስቴትስ ባለው አትላንቲክ ካውንስል የአፍሪቃ ማእከል ስራ አስኪያጅ ጄ ፒተር ፋም

አይቮሪ ኮስት ላይ ትላንት እሁድ የተፈጸመው ጥቃት አል-ቃዒዳ በሀገሪቱ እየታየ ያለውን የፖሊቲካ መረጋጋትና የኢኮኖሚ እድገት ለማሰናከል የሚያድርገው ጥረት ተደርጎ መታየት አለበት ሲሉ አንድ የአፍሪቃ ጉዳይ ጠቢብ ተናግረዋል።

በዩናይትድ ስቴትስ ባለው አትላንቲክ ካውንስል የአፍሪቃ ማእከል ስራ አስኪያጅ ጄፒተር ፋም (J Peter Pham) አይቮሪ ኮስት ካለፉት አራት አመታት ወዲህ ያሳየችው መሻሻል ሁሉ በዐል-ቓዒዳ ተግባር ምክንየት ከተሰናከል በጣም ያሳዝናል ብለዋል። ዩናይትድ ስቴትስና የአይቮሪኮስት ቅኝ ገዢ የነበረችው ፈረንሳይ ራሳቸውን ለመቻል በመጣጣር ያሉትን የፍሪቅ ሀግሮች መርዳት ይኖርባቸዋል ብለዋል።

ፋይል ፎቶ - በዩናይትድ ስቴትስ በሚገኝ አትላንቲክ ካውንስል የአፍሪቃ ማእከል ስራ አስኪያጅ ጄፒተር ፋም
ፋይል ፎቶ - በዩናይትድ ስቴትስ በሚገኝ አትላንቲክ ካውንስል የአፍሪቃ ማእከል ስራ አስኪያጅ ጄፒተር ፋም

“በአይቮሪ ኮስት ላይ የተፈጸመው ጥቃት መወገዝ አለበት። አል-ቃዒዳ በእስላማዊ መግረብና አጋሮቹ ሰላማዊ ሰዎችን በመፍጀት ተግባራቸው ምን ያህል ጨቃኞች እንደሆኑ ያሳያል" ሲሉም አክለዋል።

በአይቮሪ ኮስት ላይ ጥቃት የተፈጸመው በሀገሪቱ የፖለቲካ መረጋጋት ስለሌለና በዘሮች መካከል ውጥረት ስላለ አይደለም። እንዳውም ሀገሪቱ ካለፉት አራት አመታት ወዲህ ጥሩ እርምጃ ስታካሄድ ቆይታለች ሲሉ አስረድተዋል።

XS
SM
MD
LG