በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኒው ዮርክ ውስጥ የታሰበ የጥቃት ዕቅድ ከሸፈ


የዩናይትድ ስቴትስ ፍርድ ቤት በዋሽንግተን ዲሲ ፋይል ፎቶ
የዩናይትድ ስቴትስ ፍርድ ቤት በዋሽንግተን ዲሲ ፋይል ፎቶ

የእስልምና መንግሥት ነኝ በሚለው ቡድን ስም ሰላማዊ ሰዎችን ለመግደል በማሴር የተወነጀለ የኒውዮርክ ክፍለ ሀገር ነዋሪ ታስሯል።

በትናንትናው የአውሮፓውያን አዲስ ዓመት ዋዜማ ላይ የእስልምና መንግሥት ነኝ በሚለው ቡድን ስም ሰላማዊ ሰዎችን ለመግደል በማሴር የተወነጀለ አንድ የኒው ዮርክ ክፍለ ሀገር ነዋሪ መታሰሩን የዩናይትድ ስቴትስ የፍርድ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሐሙስ ጠዋት ፍርድ ቤት የቀረበው የሃያ ኣምስት ዓመቱ ኢማኑኤል ለችማን ለአይ ሲ ል የማቴሪያል ድጋፍ ለመስጠት በመሞከር ወንጀል ክስ ተመስርቶበታል።

ሃይማኖቱን ወደእስልምና መቀየሩን ራሱ የሚናገረው ኢማኑኤል ከ2006 ዓመተ ምህረት ጀምሮ የወንጀል ተግባር ታሪክ ያለው ካሁን ቀደምም በአእምሮ ሁከት ምክንያት ታስሮ እንድነበር መግለጫው አስታውቋል።

በውጭ ካለ የእስልምና መንግሥት አባል በተሰጠኝ መመሪያ መሥረት ኒውዮርክ ሮቼስተር አካባቢ በሚገኝ ምግብና መጠጥ ቤት በሲቪሎች ላይ በማሳሪያ ጥቃት ላደርስ ዕቅድ አለኝ ማለቱ በክሱ ዶሴ ተዘርዝሩዋል።

ጩቤ፡ ቆንጨራ፡ ማሸጊያ ቴፖችና የበረዶ ተንሸራታቾች የፊት መሸፈኛ አዘጋጅቶ እንደነበርም ተገልጿል። የዜና ዘገባችንን ለማዳመጥ የድምጽ ፋይሉን ይጫኑ።

ኒው ዮርክ ውስጥ የታሰበ የጥቃት ዕቅድ ከሸፈ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:40 0:00

XS
SM
MD
LG