በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚደንት ትረምፕ ለኢራን ተቃዋሚዎች መልዕክት አስተላለፉ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ለኢራን ተቃዋሚዎች ባስተለፉት መልዕክት፣ "በቴህራኑ ጨቋኝና ነፍሰ ገዳይ አምባገነን አገዛዝ ላይ መነሳታችሁ ይበል የሚያሰኝ ነው" በማለት አወደሷቸው። የኢራን መንግሥት ግን ተዋሚዎቹን በጠላትነትና በፀረ መንግሥነት መፈረጁ ተገልጧል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ለኢራን ተቃዋሚዎች ባስተለፉት መልዕክት፣ "በቴህራኑ ጨቋኝና ነፍሰ ገዳይ አምባገነን አገዛዝ ላይ መነሳታችሁ ይበል የሚያሰኝ ነው" በማለት አወደሷቸው። የኢራን መንግሥት ግን ተዋሚዎቹን በጠላትነትና በፀረ መንግሥነት መፈረጁ ተገልጧል።
ባለፈው ሳምንት ማብቂያ በመላ ኢራን ውስጥ በተጀመረው ፀረ መንግሥት ተቃውሞ፣ ትናንት ሌሊቱን አሥር ሰዎች እንደተገደሉ፣ መንግሥታዊው ቴሌቪዥን መዘገቡ ይታወሳል።
ዘገባው፣ ሟቾችን በተመለከተ የሰጠው ዝርዝር የለም።

ትናንት ሰኞ ማለዳ አካባቢ ዒልኝዓ የዜና አውታር አንድ የምክር ቤት አባል የተናገሩትን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ ሁለት ሰዎች ሌሊቱን በተካሄደ ተኩስ ዒዘህ ከተማ ውስጥ ተገድለዋል። ለግድያው ማን ተጠያቂ እንደሆነ ግን አላብራራም።
የወቅቱ አመጽ የተቀሰቀሰው ባለፈው ሐሙስ "ማሽሃድ" በተባለችውና የፕሬዚደንቱ ሐሰን ሮሃኒም የትውልድ ስፍራ በሆነችው ከተማ በተካሄደ አነስተኛ የተቃውሞ ሰልፍ መሆኑም ታውቋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG