በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሀሪኬን ኧርማ የተፈናቀሉ የፍሎሪዳ ነዋሪዎች ወደ የቤቶቻቸው እየተመለሱ ነው


ኃይለኛ ዝናብ ቀላቅሎ በሚነፍሰው ሀሪኬን ኧርማ ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ የፍሎሪዳ ነዋሪዎች፣ ዛሬ ማክሰኞ ወደየቤቶቻቸው መመለስ መጀመራቸው ተሰማ።

ኃይለኛ ዝናብ ቀላቅሎ በሚነፍሰው ሀሪኬን ኧርማ ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ የፍሎሪዳ ነዋሪዎች፣ ዛሬ ማክሰኞ ወደየቤቶቻቸው መመለስ መጀመራቸው ተሰማ።

መልሶ የማቋቋሙ ሥራ ግን ባጭሩ የሚቋጭ እንዳልሆነና ጊዜም የሚፈልግ መሆኑን ባለሥልጣናት አልሸሸጉም።

በአውሎ ንፋሱ ኧርማ የደረሰው ውድመት፣ በተለይም በአንዳንድ ስፍራዎች፣ ከሚገመተው በላይ እንደሆነ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ በትዊተር አመልክተው፣ በሥራው የተሰማሩት ሰዎች ደግሞ አስደናቂ ተግባር እያከናወኑ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

የአስቸኳይ ጊዜ ሠራተኞች ቡድን፣ በጎርፍ ከተጥለቀለቁ አካባቢዎች በየአያሌ ሰዎችን ሕይወት እንዳዳኑ፣ መንገዶችን እንደጠገኑ፣ ፍርስራሾችን እንደሰበሰቡና በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ነዋሪዎችና የንግድ ተቋማትም የኤሌክትሪክ ብርሃን እንዲያገኙ ማድረጋቸው ታውቋል።

የፌዴራሉ የአስቸኳይ አስተዳደር ኃላፊ ብሮክ ሎንግ እንደተናገሩት፣ በተለይም፣ 3/4ኛ ያህሉ ቤቶች የተረመረሙበትንና 65% የሚሆነው ክፍል ውድመት የደረሰበትን እንደ ፍሎሪዳ ኪይስ የመሳሰሉትን አካባቢዎች መልሶ መገንባት እጅግ አዳጋች ነበር።

ኪይስ ውስጥ የሚገንኝ እያንዳንዱ ቤት፣ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ምንገድ ጉዳት ደርሶበታል ሲሉም፣ ብሮክ ሎንግ ተናግረዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG