በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኸሪከን ኧርማ ቢለዝብም አደገኛ ነው


ኧርማ ተብሎ የተሰየመው ዝናብ የቀላቀለ እጅግ ኃይለኛ የውቅያኖስ ማዕበል ዛሬ፤ ሰኞ ረገብ ብሎ ሰሜን ፍሎሪዳና ደቡባዊ ጆርጅያን እያዳረሰ ነው።

ኧርማ ተብሎ የተሰየመው ዝናብ የቀላቀለ እጅግ ኃይለኛ የውቅያኖስ ማዕበል ዛሬ፤ ሰኞ ረገብ ብሎ ሰሜን ፍሎሪዳና ደቡባዊ ጆርጅያን እያዳረሰ ነው።

ምንም እንኳ ኧርማ ቀለል ባለ ማዕበልነት ቢፈረጅም የአደገኛነቱ ሥጋት ግን አሁንም እጅግ የበረታ ነው።

ማዕበሉ አሁንም የደቡባዊ ምሥራቅ የባሕር ጠረፍ አካባቢዎችን በብርቱ ሊጎዳና ወደቦችን ሊያወድም የሚችል ኃይል እንዳለው የሃገሪቱ የዩናይትድ ስቴትስ የኸሪከን ማዕከል አስታውቋል።

ማዕከሉ በተጨማሪም ኧርማ አውሎ ነፊስ በሰሜን ምሥራቅ ፍሎሪዳ፣ ደቡባዊ ምሥራቅ ጆርጅያና ደቡብ ካሮላይና ውስጥ ከባድ ማዕበልና ጎርፍ ሊያስከትል እንደሚችል አሳስቧል።

በማዕበሉ አካባቢ ካሉ ኢትዮጵያዊያን አንዱ ከቪኦኤ ጋር ቃለ ምልልስ አድርገዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ኸሪከን ኧርማ ቢለዝብም አደገኛ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:03 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG