በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሀሪኬን ኢርማ - በሰሜን ፍሎሪዳና ደቡባዊ ጆርጂያ

ኢርማ በመባል የተሰየመው ዝናብ የቀላቀለ ኃይለኛ አውሎነፋስ ዛሬ ሰኞ ወደ ቀላል ማዕበል ተለውጦ ሰሜን ፍሎሪዳና ደቡባዊ ጆርጂያን ማዳረሱ ተሰማ።

ኢርማ በመባል የተሰየመው ዝናብ የቀላቀለ ኃይለኛ አውሎነፋስ ዛሬ ሰኞ ወደ ቀላል ማዕበል ተለውጦ ሰሜን ፍሎሪዳና ደቡባዊ ጆርጂያን ማዳረሱ ተሰማ።

ምንም እንኳ በቀላል ማዕበልነት ቢፈረጅም አደገኛነቱ እንዳለ መሆኑ ታውቋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ የሀሪኬን ማዕከል እንዳስጠነቀቀው፣ ኢርማ አሁንም የደቡባዊ ምሥራቅ ዩናይትድ ስቴትስ የባሕር ወደቦችን ሊያወድም የሚችል ኃይል አለው።

የሀሪኬን ማዕከሉ በተጨማሪም፣ ኢርማ አውሎ ነፋስ በሰሜን ምሥራቅ ፍሎሪዳ፣ ደቡባዊ ምሥራቅ ጆርጂያና ደቡብ ካላይና ውስጥ ከባድ ማዕበል ሊያስከተል እንደሚችል አስታውሷል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG