በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዛሬው የኢሬቻ በዓል በተፈጠረው ግጭት በመቶዎች የሚቆጠር ህይወት መጥፋቱን ኦፌኮ አስታወቀ


በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ ኃይቅ ሊከበር በዝግጅት ላይ የነበረው እሬቻ በዓል ላይ የተነሳ ተቃውሞ
በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ ኃይቅ ሊከበር በዝግጅት ላይ የነበረው እሬቻ በዓል ላይ የተነሳ ተቃውሞ

በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ ኃይቅ ሊከበር በዝግጅት ላይ የነበረውና ከኦሮሞ ክብረ በዓሎች አንዱ የሆነው እሬቻ በዓል ተስተጓጉሏል፤ በግጭትና በትርምሱ ወቅት ብዙ ሕይወት መጥፋቱና በአካልም ላይ ብዙ ጉዳት መድረሱ ተነግሯል፡፡

በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ ኃይቅ ሊከበር በዝግጅት ላይ የነበረውና ከኦሮሞ ክብረ በዓሎች አንዱ የሆነው እሬቻ በዓል ተስተጓጉሏል፤ በግጭትና በትርምሱ ወቅት ብዙ ሕይወት መጥፋቱና በአካልም ላይ ብዙ ጉዳት መድረሱ ተነግሯል፡፡

የመንግሥት ባወጣው መግለጫ ለበዓሉ መስተጓጎልና ለሕይወት መጥፋት “ሁከት ፈጣሪ ኃይሎች” ያላቸውን ወንጅሏል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ - ኦፌኮ በሰጠው መግለጫ መንግሥትን የተቃወሙ ባላቸው ወጣቶችና በመንግሥት ኃይሎች መካከል በተፈጠረ ግጭት በዓሉ ተቋርጦ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወት ማለፉን አስታውቋል።

ፓርቲያቸው አጠናቅሮታል ያሉትን መረጃ መሠረት ያደረጉት የኦፌኮ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃል “በሕይወት ላይ ጉዳት የደረሰው በተኩስ፣ በአስለቃሽ ጭስ እና በመረጋገጥ ነው” ብለዋል፡፡

የቆሰሉ ብዙ ሰዎች አሁንም ሆስፒታል እንደሚገኙ አክለው የተናገሩት ዶ/ር መረራ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል አመልክተዋል።

በሌላ በኩል የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ቦታው እንደነበሩና የዐይን እማኝ መሆናቸውን የገለፁ ሰዎች “ግጭቱ የተጀመረው በበዓሉ መክፈቻ ላይ ንግግር ሊያደርጉ በነበሩ ሰዎች ላይ እና ሊሰቀል በነበረ ባንዲራ ላይ ተቃውሞ በመነሳቱ ነው” ብለዋል፡፡

ግጭቱ ከተፈጠረ በኋላም ብዙ ሰው በተኩስ፣ በአስለቃሽ ጭስ፣ በመረጋገጥ እና ገደል ውስጥ ገብቶ ብዙ ሕይወት መጥፋቱን ገልፀዋል።

የተጎዱ ሰዎችን በተመለከተ እስካሁን ይህ ነው የተባለ ትክክለኛ ቁጥር ማግኘት ባይቻልም ዐይተናል ያሉ ሰዎች ተጎጂዎች 25 በሚሆኑ መኪኖች መወሰዳቸውን ጠቁመዋል፡፡

የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ጽ/ቤት በሰጠው መግለጫ “የእሬቻ በዓልን ባህላዊ አከባበር ጠብቆ ለማክበር የኦሮሞ ህዝብ አባገዳዎችና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ያደረጉት ሰፊ ዝግጅት አስቀድመው የተዘጋጁ ባላቸው ኃይሎች ሁከትና ግርግር ተስተጓጉሏል” ብሏል፡፡

ስለጠፋው ሕይወት መንግሥት የተሰማውን ኀዘን የገለፀው የፅ/ቤቱ መግለጫ ሕይወት የጠፋውም “ሁከት ፈጣሪዎቹ ባስነሱት ሁከት በተፈጠረ ግርግር ተገጋግጠው ነው” ብሏል።

“ሁከት ፈጣሪ” ስላላቸው ወገኖች ማንነትና በሕይወትና በአካል ላይ ስለደረሰው ጉዳት ፅ/ቤቱ ዝርዝር መግለጫ አልሰጠም፡፡

ጽዮን ግርማ ዝርዝር አላት።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምፅ ያድምጡ

በዛሬው የኢሬቻ በዓል በተፈጠረው ግጭት በመቶዎች የሚቆጠር ህይወት መጥፋቱን ኦፌኮ አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:17:42 0:00

XS
SM
MD
LG