አዲስ አበባ —
የፊታችን ዕሁድ፤ መስከረም 22 በኦሮሞ ማኅበረሰብ የሚከበረው የእሬቻ በዓል ያለጣልቃገብነት ሕዝባዊ በዓል ሆኖ እንዲከበር ተቃዋሚው የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ - ኦፌኮ ጥሪ አስተላልፏል።
ኦፌኮ “በእሬቻ በዓል ስም የፖለቲካም ሆነ የግል ፍላጎቶቻቸውን በህዝብ ላይ ለመጫን እየሞከሩ ነው” ሲል የገዥውን ፓርቲና የክልሉን መንግሥት አመራር ከስሷል።
ኦፌኮ በመግለጫው የበዓሉ ታዳሚዎች ባለፈው ዓመት በተካሄዱ ሰላማዊ ሰልፎች የተገደሉ ሰዎችን በማሰብ በዝምታና በመዝሙር እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርቧል፡፡
የክልሉ መንግሥት ሃሣቡን ለቪኦኤ እንደሚሰጥ አስታውቋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡