በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለመሆኑ የከፍተኛ ፍርድቤቱ አሰራር ምን ይመስላል?


ለመሆኑ የከፍተኛ ፍርድቤቱ አሰራር ምን ይመስላል?
ለመሆኑ የከፍተኛ ፍርድቤቱ አሰራር ምን ይመስላል?

በአሁኑ ወቅት በዩናይትድ ስቴይትስ የእድሜ ዘመን የዳኝነት ሹመት አሰራር ላይ ሕዝባዊ ክርክር እየተካሄደ ነው። አንዳንድ ባለሙያዎች እንዲያውም የሕገ-መንግስታዊ መሻሻል እንዲደረግ እየጠየቁ ነው። የስልጣን ዘመኑ ገደብ ይበጂለት ሲሉ ይሞግታሉ።

ለህይወት ዘመን የተረጋገጠ ስራ ያላቸው። ማለት የማይሻር፣ የማይቀለበስ ሀላፊነትና ስልጣን ያላቸው ሰዎች ጥቂት ናቸው።

በዩናይትድ ስቴይትስ እንዲህ ያለ ስልጣን ያለው ከዳኞች ሁሉ የበላይ የሆነው የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኝነት ነው። ወይ በሞት ወይንም ደግሞ በራስ ፈቃድ ካልሆነ፤ ይሄ ሹመት ለህይወት ዘመን ነው። በእርግጥ አንድ ጊዜ ብቻ በ1805 ሹም ሽር ተካሂዷል።

ለመሆኑ የከፍተኛ ፍርድቤቱ አሰራር ምን ይመስላል?
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:19 0:00

በአሁኑ ወቅት በዩናይትድ ስቴይትስ የእድሜ ዘመን የዳኝነት ሹመት አሰራር ላይ ሕዝባዊ ክርክር እየተካሄደ ነው። አንዳንድ ባለሙያዎች እንዲያውም የሕገ-መንግስታዊ መሻሻል እንዲደረግ እየጠየቁ ነው። የስልጣን ዘመኑ ገደብ ይበጂለት ሲሉ ይሞግታሉ። ለመሆኑ የከፍተኛ ፍርድቤቱ አሰራር ምን ይመስላል?

በዩናይትድ ስቴይትስ ታላቁ ችሎት የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ነው። ዘጠኝ ዳኞች በሀገሪቱ የበላይ የሆኑ ህጎችን ያጸድቃሉ፤ ይተረጉማሉ።

ዘጠኙ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች፤ በሌሎች ፍርድ ቤቶች በተወሰኑ ውሳኔዎች ላይ የመጨረሻ ፍርድ ያሳልፋሉ።

በዚህ ምክንያት ዳኞቹ እጅግ ሰፊ ስልጣን አላቸው። የሕዝቡን ኑሮ በቀጥታ የሚመለከቱና የሀገሪቱን አቅጣጫ የሚለውጡ ወይንም የሚያጸኑ ውሳኔዎችን ያጸድቃሉ።

ስልጣናቸው ደግሞ የጊዜ ገደብ የለውም! እስከ እድሜያቸው ፍጻሜ ድረስ።

የዩናይትድ ስቴይትስ ሕገ-መንግስት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች ሹመት ለእድሜ ልክ ነው አይልም። ነገር ግን አንቀጽ ሶስት የተተረጎመው እንደዚያ ነው።

አንቀጽ ሶስት ንዑስ አንቀጽ አንድ፡- “የጠቅላይ ፍርድ ቤትና የበታች ፍርድ ቤት ዳኞች በጥሩ ስነ-ምግባር በስልጣናቸው ይቆያሉ”(አንድ ጊዜ ብቻ በ1805 ሹም ሽር ተካሂዷል)

ዳኞቹ ስልጣናቸው እድሜልክ እንዲቆይ የተደረገው፤ ውሳኔዎቻቸው በፖለቲከኞች እንዳይሸበቡ ነው።

የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች በፍትህ ስርዓቱ በገለልተኝነት ያገለግላሉ። ሆኖም የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች የሚሾሙት በፖለቲከኞች ነው።

ሹመቱን የሚሰጡት ፕሬዝደንቶች ዳኞቹን ሲሾሙ በፖለቲካ አስተሳሰባቸው መርጠው ነው።

አዲሱን ክፍለ-ዘመን ከጀመርን አንስቶ ዳኞቹ ድምጽ የሚሰጡት በግል እምነቶቻቸው ተነስተው ነው፤ አንድ ጥናት እንዳመለከተው 98 ከመቶው።

ከ1970ዎቹ እስከ 2006 እ.አ.አ. በአማካይ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኞች ለ26 ዓመታት በስልጣን ቆይተዋል።

አንዳንድ ጊዜ በፈቃዳቸው ጡረታ የሚወጡ ዳኞች በፖለቲካ አመለካከት የሚቀርባቸው ፕሬዝደንት እስኪመረጥ ድረስ ጡረታቸውን ያዘገያሉ።

በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ከዘጠኙ ዳኞች በሞት ወይንም በጡረታ አንዱ/አንዷ ሲገለሉ፤ ክፍተቱን ለመሙላት የሚከናወነው ሂደት፤ በፖለቲካ አመለካከት የተውሰበሰበ ነው።

XS
SM
MD
LG