በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአሜሪካ ጠቅላይ ዳኛ ሹመት ዙሪያ ያለው እሰጥ-አገባ


ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኛ አንተኒ ስካሊያ ሞት ምክንያት የተፈረውን ባዶ ቦታ ለመሙላት ሕግ በሚያዝዛቸው መሠረት ትናንት ሜርሊክ ጋርላንድን መርጠው አሳውቀዋል።

ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኛ አንተኒ ስካሊያ ሞት ምክንያት የተፈረውን ባዶ ቦታ ለመሙላት ሕግ በሚያዝዛቸው መሠረት ትናንት ሜርሊክ ጋርላንድን መርጠው አሳውቀዋል።

ፕሬዚዳንቱ ዳኛ ጋርላንድ ምርጫቸው መሆናቸውን ከማሳወቃቸው በፊት ከሪፐብሊካኑም ከዴሞክራቶቹም የሕዝብ እንደራሴዎች፣ እንዲሁም ከዳኝነት ጉዳዮች ሊቃውንት ጋር መምከራቸውን በቤተ መንግሥቱ ሮዝ መናፈሻ ውስጥ ንግግር ባደረጉበት ጊዜ ገልፀዋል።

የሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ ሪፐብሊካን አባላት የተሰናባች፣ የሥልጣን ዘመኑ ሊጠናቀቅ ከአንድ ዓመት ያነሰ ጊዜ የቀረው ፕሬዚዳንት ያቀረበውን ዕጩ ሹመት ጨርሶ እንደማያዩ ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንቱ ግን እንደራሴዎቹ ይህንን አቋማቸውን ተመልሰው እንዲፈትሹና የዕጩአቸውን ጉዳይ እንዲመለከቱ በአፅንዖት ጠይቀዋል።

ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ዳኛ ሜሪክ ጋርላንድን ለጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ማጨታቸውን ካሳወቁ በኋላ የተናገሩት የሪፐብሊካን ፓርቲው የሴኔቱ መሪ ሚች ማክኮኔል የፕሬዚዳንቱን ዕጩ ጉዳይ እንደማያዩ በድጋሚ አረጋግጠዋል።

ለህይወት ዘመን የተረጋገጠ ሥራ፣ የማይሻር፣ የማይቀለበስ ኃላፊነትና ሥልጣን ያላቸው ሰዎች ጥቂት ናቸው። በዩናይትድ ስቴትስ እንዲህ ያለ ሥልጣን ያለው የዳኝነት ሁሉ የበላይ የሆነው የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኝነት ነው። ወይ በሞት አልያም በራስ ፈቃድ ካልሆነ ይህ ሹመት የህይወት ዘመን ሹመት ነው።

በዩናይትድ ስቴትስ የዕድሜ ዘመን የዳኝነት ሹመት አሠራር ላይ ሕዝባዊ ክርክር እየተካሄደ ነው። አንዳንድ ባለሙያዎች እንዲያውም ሕገ-መንግስታዊ ማሻሻያ እንዲደረግ እየጠየቁ ነው። የሥልጣን ዘመኑ ገደብ ይበጅለት ሲሉ ይሟገታሉ። ለመሆኑ የከፍተኛ ፍርድቤቱ አሰራር ምን ይመስላል?

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በአሜሪካ ጠቅላይ ዳኛ ሹመት ዙሪያ ያለው እሰጥ-አገባ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:25 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG