በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኦባማ ዕጩ ዳኛ መረጡ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኛ እንዲሁኑ የፌደራሉን ይግባኝ ሰሚ ችሎት ዳኛ ሜሬዲክ ጋርላንድን መርጠው አቀረቡ።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኛ እንዲሁኑ የፌደራሉን ይግባኝ ሰሚ ችሎት ዳኛ ሜሬዲክ ጋርላንድን መርጠው አቀረቡ።

ፕሬዚዳንቱ ዳኛ ጋርላንድን የመረጡት በቅርቡ ያረፉትን አንተኒን ስካልያን እንዲተኩ ነው።

ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ምርጫቸውን ያሳወቁት ዛሬ ረፋድ ላይ በቤተመንግሥታቸው አፀድ በሚገኘው ሮዝ መናፈሻ ውስጥ ነው።

አንድ በዚያ ዳኛ ስካሊያ ጥለውት ባለፉት መንበር የሚሞላ ሰው ሲፈልጉ ላይና ታች ሲሉ ሣምንታትን ማስቆጠራቸውን ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል።

ኦባማ ዕጩ ዳኛ መረጡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:02 0:00

“እናም ዛሬ - አሉ ፕሬዚዳንት ኦባማ - ይህንን ሁሉንም አማራጮችን ያየሁበትን ሂደት አሳውቄ ውሣኔዬ ላይ ደርሻለሁ። ከአሜሪካ እጅግ የሰሉ የሕግ አዕምሮዎች አንዱ የሆኑትን ብቻ ሳይሆን የክብር፣ የትህትና፣ የመልካም ተክለ-ሰብዕና፣ የፍትሐዊነትና የምጡቅነትን የሥራ መንፈስ የሚዘሩብንን ሰው ዕጩ አድርጌ መርጫለሁ።”

ይሁን እንጂ የሥልጣን ዘመናቸው ሊያበቃ ዘጠኝ ወራት የቀሯቸውን የኦባማን የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዕጩ ዳኛ ሹመት እንደማያፀድቁ፤ እንዲያውም ጉዳያቸውንም ለውይይት እንደማያቀርቡ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱን አብላጫ መቀመጫ የያዙት ሪፐብሊካን እንደራሴዎች ዝተዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ኦባማ ዕጩ ዳኛ መረጡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:15 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG