በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰነተር ቲሞቲ ከይን የዲሞክራቲክ ፓርቲ እጩ ምክትል ፕሬዝደንት ሆነው ተመረጡ


በ2016ቱ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ የዲሞክራቲክ ፓርቲ ታሳቢ እጩ ሂላሪ ክሊንተን የቨርጂናውን ሰነተር ቲሞቲ ከይን ምክትል ፕረዝደንት ሆነው እንዲወዳደሩ መርጠዋቸዋል።

ሰነተር ከይን ከአሁን በፊት የክፍለ ግዛት አስተዳዳሪ እና የዲሞክራቲክ ፓርቲ ጉባዔ ሊቀመንበር ሆነው ያገለገሉ ሲሆኑ ባላቸው የስጳኛ ቋንቋ ችሎታ ደግሞ ሂላሪ ክሊንተን የላቲን አሜሪካዊያን ተወላጆች ድምፅን ለማግኘት ይረዱዋቸዋል ተብሎ ይግመታል።

ዲሞክራቲክ ፓርቲ በ2016ቱ ምርጫ ፓርቲውን ወክሎ የሚወዳደርን እጩ ለመምረጥ ከሃምሌ 25-28 በፊላደልቭያ ፔንስልቫንያ ጉባዔ ያካሂዳል።

XS
SM
MD
LG