በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጀርመን የአውሮፓው ሼንገን ቀጣና አደጋ ላይ መሁኑን አስጠነቀቀች


ጊዝያዊ አጥር በሃሊየ የባቡር ጣብያ (Hyllie train station)ደቡብ ማልሞ ስዊድን (Malmo, Sweden)ውስጥ እአአ 2016. [ፎቶ ሮይተርስ/REUTERS]
ጊዝያዊ አጥር በሃሊየ የባቡር ጣብያ (Hyllie train station)ደቡብ ማልሞ ስዊድን (Malmo, Sweden)ውስጥ እአአ 2016. [ፎቶ ሮይተርስ/REUTERS]

ፓስፖርት የማያስፈልገው የአውሮፓው ሼንገን ቀጣና አደጋ ላይ መሆኑን ጀርመን አስጠነቀቀች፡፡

ጀርመን ይህንን ማስጠንቀቂያ ይፋ ያደረገችው ፍልሰተኞችን ለመቆጣጠር በሚል ስዊድንና ዴንማርክ አዲስ የድንበር መቆጣጠሪያ ሕግ በማውጣታቸው እንደሆነም ታውቋል፡፡

የጀርመኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማርቲን ሼፈር “የቦታ ቦታ የመዘዋወር ነፃነት ጠቃሚ መመሪያ መሆኑን አመልክተው ይህም የአውሮፓ ኅብረት ካስገኛቸው ውጤቶች ትልቁ ነው” ብለዋል፡፡

የጀርመኑ ባለሥልጣን ይህንን የተናገሩት ዴንማርክ ከጀርመን ጋር የሚያዋስናትን ድንበር እንደምትዘጋ ከገለፁ ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ነው፡፡

የደንማርኩ ጠቅላይ ሚኒስትር ላርስ ሎክ ራስሙሰን በበኩላቸው “በሌሎቹ የኖርዲክ ሃገሮች የሚታየው ሁኔታ ጥገኝነት የሚሹ ብዙ ፍልሰተኞች ወደ ሃገራቸው እንዲጎርፉ ያደርጋል” ብለዋል፡፡

ስዊድን ዛሬ ይፋ ያደረገችው አዲስ ሕግ ከዴንማርክ የሚገቡ መንገደኞች ፎቶግራፋቸው ያለበት መታወቂያ እንዲያሳዩ ይደነግጋል፡፡ የዜና ዘገባችንን ለማዳመጥ የድምጽ ፋይሉን ይጫኑ።

ጀርመን የአውሮፓው ሼንገን ቀጣና አደጋ ላይ መሁኑን አስጠነቀቀች
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:09 0:00

XS
SM
MD
LG