በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የማዕከላዊ አፍሪቃ ሬፓብሊክ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትሮች በፕሬዚደንታዊ የመለያ ምርጫ ከባድ ፉክክር እንደሚገጥማቸው ተገለጸ


እአአ 2015 ባለፈው ትኅሣሥ 30 ቀን የተካሄደ የመጀመሪያ ዙር ውድድር ሰዎች ተሰልፈው - ፋይል ፎቶ
እአአ 2015 ባለፈው ትኅሣሥ 30 ቀን የተካሄደ የመጀመሪያ ዙር ውድድር ሰዎች ተሰልፈው - ፋይል ፎቶ

ማዕከላዊ አፍሪቃ ሬፓብሊክ ፕሬዚደንታዊና ምክር ቤት ምርጫ እያካሄደች መሆኗ ይታወቃል።

ሁለት የማዕከላዊ አፍሪቃ ሬፓብሊክ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትሮች፣ እአአ ለመጭው 31 ቀን 2016 ዓ.ም. በታቀደው ፕሬዚደንታዊ የመለያ ምርጫ ከባድ ፉክክር እንደሚገጥማቸው ተገለጸ።

ባለፈው ሐሙስ ይፋ የሆነው ጊዜያዊ የመጀመሪያ ዙር ውጤት እንዳመለከተው አኒሰት ጊዮርጊስ ዶሎጉለ (Anicet Georges Dologuele) በ24% ድምፅ የመሪነቱን፣ ፋውስቲን አርቻንጅ ቶዋደራ (Faustin Archange Touadera) ደግሞ በ19% ድምፅ የሁለተኛነቱን ስፍራ ይዘዋል።

እአአ ባለፈው ትኅሣሥ 30 ቀን በተካሄደው የመጀመሪያ ዙር ውድድር ከ30 በላይ እጩዎች መቅረባቸው ይታወሳል። ብሔራዊው የምርጫ ባለሥልጣን እንዳመለከተው ከሆነ፣ በከፍተኛ ደረጃ የሚጠበቀው የድምፅ አሰጣጥ 79% ደርሷል።

ባለፈው ሳምንት ውስጥ አንድ የተወዳዳሪዎች ቡድን፣ ምርጫው መጭበርበርና አንዳንድ የሎጂስቲክስ ጉድለቶች ስለነበሩት እንዲሰረዝ መጠየቁ ይታወሳል። ብሔራዊ የምርጫ ባለሥልጣን ግን ጥያቄያቸው ተቀባይነት የለውም በሚል ውድቅ አድርጎታል።

ማዕከላዊ አፍሪቃ ሬፓብሊክ፣ ሽምቅ ተዋጊዎች ፕሬዚደንት ፍራንሷ ቦዚዜን (Francois Bozize) ከሥልጣን ካስወገዱ ከዓመት በኋላ ማለትም እአአ በ2014 የተቋቈመውን ጊዜያዊ መንግሥት ለመተካት፣ ፕሬዚደንታዊና ምክር ቤት ምርጫ እያካሄደች መሆኗ ይታወቃል።

የዜና ዘገባውን ለማዳመጥ ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ፋይል ይጫኑ።

XS
SM
MD
LG