በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመካከለኛ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዚደንታዊና ምክር ቤታዊ ምርጫ ተጀምሯል


ምርቻውን ብዙዎች በበሀገሪቱ በክርስቲያኖችና ሙስሊሞች መካከል ለሶስት ዓመት ገደማ የቀጠለውን ብጥብጥ ያከትመዋል የሚል ተስፋ ጥለውበታል።

ለረጅም ጊዜ ሲጓተት የቆየው የመካከለኛ ኣፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዚደንታዊና ምክር ቤታዊ ምርጫ ተጀምሯል። ምርቻውን ብዙዎች በበሀገሪቱ በክርስቲያኖችና ሙስሊሞች መካከል ለሶስት ዓመት ገደማ የቀጠለውን ብጥብጥ ያከትመዋል የሚል ተስፋ ጥለውበታል።

በዋና ከተማዋ ባንጊ ድምጽ ለምስተት በረጃጅም ሰልፎች የሚጠባባቁ መራጮች የታዩ ሲሆን ኣንዳንድ ጣቢያዎች ዘግየት ብለው ከመከፈታቸው በቀር ግጭትም ሆነ ከባድ የምርጫ ሂደት መዛባት ሪፖርት ኣልተሰማም።

ባለፈው ዕሁድ ሊካሄድ ታቅዶ በቴክኒክ ዕክሎች ምክንያት ዘግይቶ ዛሬ ለተከፈተው ምርጫ ከፍተኛ የጸጥታ ጥበቃ እየተካሄደ መሆኑ ታውቁዋል።

ኣሳሳቢ በሆኑ ኣካባቢዎች የተባበሩት መንግሥታት ሰላም ኣስከባሪዎች የተሰማሩ ሲሆን ሶስት መቶ የታጠቁ ሃይሎች በዋና ከተማዋ ባንጊ በሌሎች ኣካባቢዎች ደግሞ ኣንድ ሲህ ስምንት መቶ ፖሊስና የጥበቃ ሃይሎች ተሰማርተኣዋል።

የተባባሩት መንግስታት ዋና ጸሓፊ ባን ኪ ሙን ሁሉም የሚመለክታቸው ወገኖች ምርቻው በሰላማዊ ኛ በተእማኒ መንገድ እንዲጠናቀቅ በቁርጠኝነት እንዲሰሩ ተማጽነዋል።

በምርጫው ሰላሳ ከሚሆኑ ፕሬዚደንታዊ ዕጩዎች እና ለምክር ቤት ተወካይነት ከሚወዳደሩ ብዛት ያላቸው ተፎካካሪዎች መካከል ለመምረጥ ከኣንድ ነጥብ ስምንት ሚሊዮን በላይ ህዝብ ተመዝግቡዋል። የዜና ዘገባችንን ለማዳመጥ ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ፋይል ይጫኑ።

የመካከለኛ ኣፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዚደንታዊና ምክር ቤታዊ ምርጫ ተጀምሯል
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:29 0:00

XS
SM
MD
LG