በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

 
ከብት እርባታ በትግራይ፡- ከፈረንጅ ላም ጋር የተዳቀሉት በቀን እስከ 36 ሊትር ወተት ይሰጣሉ

ከብት እርባታ በትግራይ፡- ከፈረንጅ ላም ጋር የተዳቀሉት በቀን እስከ 36 ሊትር ወተት ይሰጣሉ


አቶ ሰለሞን ገሰሰ የፈረንጅና የአበሻ የወተት ላሞችን በማዳቀል እስከ 36 ሌትር ወተት ማለብ ችለዋል
አቶ ሰለሞን ገሰሰ የፈረንጅና የአበሻ የወተት ላሞችን በማዳቀል እስከ 36 ሌትር ወተት ማለብ ችለዋል

ትግራይ ውስጥ ካሉት በወተት ምርት የተሰማሩ ገበሬዎች አንዱ አቶ ሰለሞን ገሰሰ ይጠቀሳሉ፡፡ አቶ ሰለሞን በ1992 ዓ/ም ከፈረንጅ ላሞች ዘር ጋራ የተዳቀሉ ሁለት ላሞችን ገዝተው ማራባት ይጀምራሉ፡፡

በአሁኑ ሰዓት የላሞቹ ቁጥር ከ130 በላይ ደርሷል፡፡ ከነዚህ ውስጥ 82 ላሞች በተለያዩ ጊዜ ሸጠዋል፡፡ ላንዷን ላም በአማካይ ከ17ሽህ እስከ 21ሽህ ብር ይሸጣሉ፡፡

ከተቀሩት ላሞች ከአንዷ ብቻ በቀን 36 ሊትር ወተት እያገኙ አንድ ሊትር በ7 ብር ለገበያ ያቀርባሉ፡፡

አቶ ሰለሞን ይህንን የላሞች እርባታ የሚያካሂዱት በትግራይ ክልል በመቀሌ ከተማ ወደ አዲስ አበባ በሚወስደው መንገድ ከመቀሌ 10 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው አነስተኛ ከተማ ኵሓ ውስጥ ባለው የመኖርያ ቤታቸው ግቢ ውስጥ ነው፡፡

“የላሞቹን ቁጥር ጨምሬ ለማርባት ሰፊ ቦታ እንዲሰጠኝ ለሚመለከተው የመንግስት አካል በተደጋጋሚ ጠይቄ እስከ አሁን አልፈቀዱልኝም፡፡ አሁን ይሰጡኛል ብዮ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡” ብለዋል አቶ ሰለሞን፡፡

ሰፊ ቦታ ከተፈቀደላቸው የወተት ውጤቶችን የሚያመርት መለስተኛ ፋብሪካ ለማቋቋምን አቅደዋል፡፡

ከመንግስት በኩል ለጥሩ አርአይነታቸው ተደጋ

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG