በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የራያና ቆቦ ገበሬዎች በድርቅ ምክንያት ከብቶቻቸውን እየሸጥን ነው ይላሉ


ራያ ቆቦ
ራያ ቆቦ

በራያና ቆቦ ልዩ ስሙ መንደፈራ በተባለ አካባቢ የሚኖሩ ገበሬዎች ምግብ ለመሸመት ከብቶቻቸውን እየሸጡ መሆኑን ይናገራሉ።

በራያና ቆቦ ልዩ ስሙ መንደፈራ በተባለ አካባቢ የሚኖሩ ገበሬዎች በምግብ እጥረት ከብቶቻቸውን እየሸጡ መሆኑን ይናገራሉ። በአካባቢው በአሁኑ ሰአት እየጣለ ያለው ዝናብ የዘሩትን እንዳያበላሽባቸው ክፉኛ ሰግተዋል። ከመንግስት በቂ የእህል እርዳታ ካላገኘን ከባድ የረሃብ አደጋ ይደርስብናል ብለው እንደሚፈሩም ተገልጿል።

በሰሜን ወሎ ዞን የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ፕሮግራም ማስተባበርያ ጽ/ቤት ተጠሪ አቶ መሃመድ ያሲን በበኩላቸው በዞኑ ለ54,000 ሕዝብ እርዳታ እንደተሰጠና መንግስት በቂ የእህል ክምችት እንዳለው ይናገራሉ።

ዘገባውን ግርማይ ገብሩ ከመቀሌ ልኮልናል ከዚህ በታች ካለው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

የራያና ቆቦ ገበሬዎች በድርቅ ምክንያት ከብቶቻቸውን እየሸጥን ነው ይላሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:42 0:00

XS
SM
MD
LG