አዲስ አበባ —
የፌዴራሉ ጠቃይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት፥ የቀድሞ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ የአመራር አባላትን እነ ሃብታሙ አያሌውን ጨምሮ ሌሎች ተከሳሾችም ከእሥር እንዲፈቱ ለአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ።
ፍርድ ቤቱ በይግባኝ የተያዘው ጉዳያቸው ውሳኔ እስኪያገኝ ተከሳሾቹ ከሃገር እንዳይወጡም አግዷል። ይህ የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት ተኩል ድረስ ተፈጻሚ አልነበረም።
መለስካተው አምሃ ዝርዝሩን ልኮልናል። ከድምጽ ፋይሉ ያዳምጡ።