በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከዐዋጁ በኋላ- ነዋሪዎች አነጋግረናል


ፎቶ ፋይል፡ በኢሬቻ በዓል ላይ ተሳታፊዎች የተቃውሞ ምልክት ሲያሳዩ
ፎቶ ፋይል፡ በኢሬቻ በዓል ላይ ተሳታፊዎች የተቃውሞ ምልክት ሲያሳዩ

መስከረም 28 ቀን 2009 ዓ.ም በኢትዮጵያ መንግሥት የታወጀውን አስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ተከትሎ ነዋሪዎች በጅምላ እየታሰሩና ቤታቸውም እየተበረበረ እንዲሁም በተለምዶ አጠራር ዲሽ በመባል የሚታወቁት የሬድዮና ቴሌቭዥን ሞገዶች መቀበያዎች የሚከታተሉበት እንዲነቅሉ እየተገደዱ መሆኑን ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡ ነዋሪዎች ይናገራሉ።

ሰዎች በጅምላ እየታሰሩ እየተወሰዱ ነው። ድብደባ አለ። ድንገተኛ የቤት ለቤት ፍተሻ አለ። መንገድ ላይ በሚደረግ ፍተሻ ስልኮቻችንን እንቀማለን የንግድ እንቅስቃሴ ማከናወን አልቻልንም። ኢሳትና ኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ(ኦ.ኤም.ኤን) የምንከታተልበትን የሬድዮና ቴሌቭዥን ሞገዶች መቀበያ ዲሽ እንድንነቅል እንገደዳለን ወይም አስቀድመን ራሳችን እንነቅላለን- አስተያየት ሰጪዎቹ ያሰሙት አቤቱታ ነው።

ፎቶ ፋይል፡ ጎንደር
ፎቶ ፋይል፡ ጎንደር

በሌላ በኩል ዐዋጁን ማስፈጸምያ መመርያ ከወጣ ወዲህ 2700 ሰዎች ከተለያየ ቦታ መታሰራቸውን ኮማንድ ፖስቱ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን የላከው መግለጫ ያሳያል።

ጽዮን ግርማ ወደ ተለያዩ ሰዎች ደውላ “ከዐዋጁ በኃላ ያላችሁበት አከባቢ ሁኔታ ምን ይመስላል?” ስትል ጠይቃለች።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ።

ከዐዋጁ በኋላ- ነዋሪዎች አነጋግረናል
please wait

No media source currently available

0:00 0:13:56 0:00

XS
SM
MD
LG