በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለመላው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለፀሎተ ሐሙስ አደረሳችሁ


በኢትዮጵያ የጸሎተ ሐሙስ አከባበር ምን ይመስላል በአሉ መቼ መከበር ጀመረ።

እስራኤላውያን በግብፅ በባርነት ለዘመናት ከኖሩበት ወደ እስራኤል ጉዞ ለመጀመር የነበራቸው የዝግጅት ጊዜ አጭር ነበር። በዚህም ምክንያት በፍጥነት የሚደርሰውን ጉልባን (ጥራጥሬ) ቀቅለውና ሰንቀው ከቀናት በኃላ የሚከበረውን የፋሲካ በአል ሳያከብሩ ጉዞን ጀምረዋል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነትም ያንን ለማስታወስ አስከዛሬ ትተገብረዋለች።

በተጨማሪ ፀሎተ ሃሙስን ለየት የሚያደርገው በመፅሃፍ ቅዱስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሃዋርያት እግር በማጠብ ትህትናን ያስተማረበት ቀን ስለሆነና የወይንጠጅን ደሜ ሲል ህብስቱን ደግሞ ስጋዬ ሲል በምሳሌ የሰውልጅ ከባርነት በደሙ ነፃ መውጣቱን ያረጋገጠበት ቀን ስለሆነ፤ ቅዱስ ቁርባንም የተመሰረተበት ቀን በመሆኑ የተለየ ቀን ያደርገዋል በማለት መጋቤ ብሉይ እዝራ ለገሰ በኢትዮጵያ የሊቃውንት ጉዳይ ሰብሳቢ ስለጸሎተ ሐሙስ አጭር ማብራሪያን ሰጥተውናል።​

መልካም የፀሎት በዓል!

በአሜሪካን ሃገር በተለይም ብዙ ሃበሻ በሚኖንርበት ዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢዋ በአልን ማክበር ምን ይመስላል? ስለ ጸሎተ ሐሙስ መስታወት አራጋው ከቪኦኤ ባልደረቦቿ ጋር በጋራ ያደረጉትን አጭር ጨዋታ ከበታች ያለውን የድምፅ ምልክት በመጫን ያድምጡ።

ለመላው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለፀሎተ ሐሙስ አደረሳችሁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:40 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG