በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ድምጽ አልባው ቅስፈት”- በምስራቅ አፍሪካ


Caption 2020-02-12 07:21:38 1
Caption 2020-02-12 07:21:38 1

በምስራቅ አፍሪካ ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ ሀገሮችን በመጉዳት ላይ ያለውን ድርቅ “ድምጽ አልባው ቅስፈት” ሲሉ የዩናይትድ ስቴይትስ ኮንግረስ አባላት የምስክር ሰሚ ሸንጎ አስችለዋል።

በትናንትናው ዕለት በኮንግረሱ የውጭ ጉዳዮች የአፍሪካ ንዑስ ኮሚቴ የምስክሮችን ድምጽ ሲሰማ፤ በተለይ እንደ ኢትዮጵያና ሶማሊያ ክፉኛ በድርቁ በተጠቁ አካባቢዎች የነፍስ አድን እርዳታ የሚያደርገው USAID በጀት ከተቀነሰ፤ ሊያስከትል የሚችለው ቀውስ በሰፊው ትንተና ተሰጥቶበታል።

በኮንግረስ ሕግ አርቃቂው የውጭ ጉዳይ የአፍሪካ ንዑስ ኮሚቴ ሊቀመንበር ክሪስ ስሚት ናቸው “ድምጽ አልባው ቅስፈት” ሲሉ የምስራቅ አፍሪካ ሁኔታን አስመልክቶ የምስክሮችን ቃል የሰሙት።

ምስራቅ አፍሪካ በከፋ ድርቅ ላይ ትገኛለች። በዐስር ሚሊዮን የተቆጠሩ ዜጎች የዕለት ጉርስ ለማግኘት እርዳታ በመጠባበቅ ላይም ይገኛሉ።

​“ሁኔታው በሀገሮች የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ አቅርቦት አምዶችና በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ትብብር ካልተያዘ፤ ውጤቱ የበርካቶችን ሕይወት ለቅስፈት የሚዳርግ አስከፊ ይሆናል” ሲሉ ባለሙያዎች ተናግረዋል።

ከምንም በላይ ባለሙያዎቹን በእጅጉ ያሳሰባቸው፤ ድርቁና ጉዳቱ እንዳለ ሆኖ፤ የዓለም አቀፍ ረድዔት ፖሊሲዎች ለውጥና የበጀት ሁኔታ ነው።

የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳድር ለኮንግረስ በቀረበው የበጀት ረቂቅ፤ የገንዘብ አቅማቸው እንደሚቀነስ ከተመዘገበው የውጭ ጉዳይ መስሪያቤቱ ጋር ተያየዞ የዩናይትድ ስቴይትስ ዓለም አቀፍ ተራዶ USAID ይገኝበታል።

የእርዳታ ድርጅቶችና መንግስታት በቅንጅት ለመስራት አቅማቸውን በማጠናከርና ተጨማሪ እርዳታ እየጠየቁ ባለበት ባሁኑ ወቅት፤ የበጀት ቅነሳ ዜና እረፍት እንደሚነሳቸው የገለጹት በUSAID የምግብና ሰላም ቢሮ ምክትል ስራ አስኪያጅ ማቲው ኒምስ ናቸው።

በUSAID የምግብና ሰላም ቢሮ ምክትል ስራ አስኪያጅ ማቲው ኒምስ
በUSAID የምግብና ሰላም ቢሮ ምክትል ስራ አስኪያጅ ማቲው ኒምስ

“ምስራቅ አፍሪካ ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ የከፋ ድርቅ ቀስፎ ይዟታል። በኢትዮጵያ፣ ሶማሊያና ኬንያ 15 ሚሊዮን ሰዎች በምግብና ውሃ እጥረት ተጎድተዋል። በብዙ አካባቢዎች የሰብልና እጽዋት ይዞታ በእጅጉ ተራቆተና ተያይዞ የተመናመነ ምርት ታይቷል። በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት ዝናብ ካልጣለ፤ ሁኔታው ወደ ከፋ ይዞታ ይሸጋገራል።” ብለዋል።

የድርቅ ሁኔታዎች ቅድመ-ማስጠንቀቂያ አሃዞች እንደሚያመለክቱት ወደ 70 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች በዓለም ዙሪያ በ45 ሀገሮች የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታና ማከፋፈያ መንገዶች ያስፈልጓቸዋል።

ሁኔታዎቹን ለመታደግ የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ እርዳታ ማስተባበሪያ መስሪያቤት OCHA 5.6 ቢሊዮን ዶላርስ እንደሚያስፈልግ በተደጋጋሚ ቢያስታውቅም፤ እስካሁን ቃል የተገባው 1.2 ቢሊዮን ዶላርስ ብቻ ነው።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

“ድምጽ አልባው ቅስፈት”- በምስራቅ አፍሪካ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:24 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG