በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ከብቶቻችን በድርቁ ምክኒያት መሞት ጀምረዋል” የቦረና ነዋሪዎች


(ፎቶ ፋይል፡ ፎቶዎቹ ከአንድ ዓመት በፊት በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተ ድርቅ እና የውሀ እጥረት ማሳያ ናቸው)
(ፎቶ ፋይል፡ ፎቶዎቹ ከአንድ ዓመት በፊት በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተ ድርቅ እና የውሀ እጥረት ማሳያ ናቸው)

በኢትዮጵያ በአምስት የተለያዩ ክልሎች ከደረሰው ድርቅ የቦረና ዞኑ የከፋ በመሆኑ ከብቶች መሞት መጀመራቸውን ነዋሪዎች ገለጹ። በጥቂት ቀናት ውስጥ ዝናብ መጣል ካልጀመረ ደግሞ ለከፋ አደጋ እንደሚጋለጡ በመግልጽ አሁን ያለውን የግጦሽ መሬት መድረቅ በ1977 ዓ.ም ከደረሰው አስከፊ ድርቅ ጋር ያያይዙታል።

በኢትዮጵያ በኦሮሚያ፣በሶማሌ፣በአማራ በደቡብ ፣በአማራ እና በአፋር በአጠቃላይ በአምስት ክልሎች በደረሰው ድርቅ 5.6 ሚሊዮን ሰው አስቸኳይ የዕለት ደራሽ እርዳታ እንደሚያስፈልገው ከዚህም ውስጥ 36 በመቶ የከፋ የድርቅ አደጋ የደረሰበት በኦሮሚያ ክልል በቦረናና ጉጂ ዞን መሆኑን መንግሥትና ለጋሽ ድርጅቶች አስታውቀዋል።

የብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር ምትኩ ካሣ በበኩላቸው በአሁኑ ሰዓት 5.6 ሚሊዮን ሕዝብ የዕለት ደራሽ እርዳታ እንደሚፈልግ፣ የከብቶችን እልቂት ለመቋቋም በአስቸኳይ ለገበያ የማቅረብ እርምጃ ለመውሰድ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

በድርቁ ምክኒያት ትምሕርት አቋርጠው የነበሩ ተማሪዎችን በትምሕርት ቤት ውስጥ በመመገብ ወደ ትምሕርት ገበታቸው እንዲመለሱ ማድረግ እንደተጀመረም ተናግረዋል።

ጽዮን ግርማ ያጠናቀረችውን ዘገባ ያድምጡ።

XS
SM
MD
LG