ሲፒጄ ትናንት ባወጣው መግለጫው የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ባለፉ ቅርብ ሣምንታት ውስጥ ሁለት ጋዜጠኞችና ሁለት የኢንተርኔት ላይ አምደኞችን ማሠራቸውን አመልክቶ ነበር፡፡
በትናንቲ የሲፒጄ መግለጨ ላይ የተጠቀሱት ጋዜጠኞች ዛሬ የታሠሩትንና ቀደም ሲልም እሥር ለይ የቆዩትን የማይጨምር ሲሆን ሲፒጄ በስም የጠራቸው በፍቃድ ኃይሉ፣ ናትናዔል ፈለቀ፣ አቤል ዋበላና አጥናፍ ብርሃኔ የሽብር ክሥ እንደተመሠረተባቸው ተሟጋቾች በማኅበራዊ ማድያ ላይ መፃፋቸውን አመልክቷል፡፡
የኦሮምያ ብሮድካስቲንግ አገልግሎቱ ጋዜጠኛ አብዱ ገዳ ያለበት እንደማይታወቅ ስፒጄ በትናንቱ መግለጫው ላይ ጠቅሶ የነበረ ቢሆንም በአንድ የአዳማ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ተይዞ እንደሚገኝና ሄደውም ያዩት ሰዎች መኖራቸውን ምንጮች ለቪአኤ ገልፀዋል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ሁኔታዎች ዓለምአቀፉን የጋዜጠኞች ደኅንነት እንደሚያሳስበው የቡድኑ የአፍሪካ ጉዳዮች መርኃግብር ዳይሬክተር አንጄላ ኲንታል ለቪኦኤ ገልፃለች፡፡
የኢትዮጵያ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ለቪኦኤ በሰጡት ቃለ-ምልልስ የሲፒጄን ክሦች አጣጥለዋል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡