በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የታሊባን ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 64 ሰዎች መሞታቸው የሀገሪቱ ባለ ስልጣናት ገለጹ

አፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል ውስጥ የታሊባን ታጣቂዎች ትናንት ጠዋት በቦምብና በጠብመንጃ ባደረሱት ጥቃት የቆሰሉ ሰዎች
አፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል ውስጥ የታሊባን ታጣቂዎች ትናንት ጠዋት በቦምብና በጠብመንጃ ባደረሱት ጥቃት የቆሰሉ ሰዎች

ታሊባኖቹ ዒላማ ያደረጉት በሀገሪቱ የስለላ ድርጅት ስር ያለ እና የመንግስት ባለስልጣናት ደህንነት ጥበቃ ኃይል መቀመጫ ሕንጻ መሆኑን ባለ ስልጣናቱ ገልጸዋል።

አፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል ውስጥ የታሊባን ታጣቂዎች ትናንት ጠዋት በቦምብና በጠብመንጃ ጥቃት አድርሰው እስካሁን በተረጋገጠው 64 ሰዎች ሲሞቱ ከሶስት መቶ ሃያ ሰባት የሚበልጡ ማቁሰላቸውን የሀገሪቱ ባለ ስልጣናት ገለጹ።

ታሊባኖቹ ዒላማ ያደረጉት በሀገሪቱ የስለላ ድርጅት ስር ያለ እና የመንግስት ባለስልጣናት ደህንነት ጥበቃ ኃይል መቀመጫ ሕንጻ መሆኑን ባለ ስልጣናቱ ገልጸዋል።

ሰዎች በጥቃቱ የተጎዱትን ሰለባዎች እየቀበሩ

አጥፍቶ ጠፊው መኪና ላይ የጫነውን ቦምብ ህንጻው በራፍ ላይ ያፈነዳ መሆኑንና ብዙ መቶ ኪሎ ግራም ፈንጂ መሆኑን የአገር ግዛት ሚኒስቴር ቃል ኣቀባይ ገልጾ የጥበቃ ጉድለት እንደነበር አምኗል።

አጥፍቶ ጠፊው መኪና ላይ የጫነውን ቦምብ ህንጻው በራፍ ላይ ነበር

ከፍንዳታው በኋላ አጥቂዎቹና የመንግስቱ የጸጥታ ሃይሎች ለበርካታ ሰዓታት ተታኩሰው አጥቂዎቹ በሙሉ መገደላቸው ተዘግቧል።

የአፍጋኒስታን ፕሬዚደንት አሽራፍ ጋኒ ጥቃቱን አጥብው ያወገዙ ሲሆን ድርጊቱ የጠላትን ሽንፈት በግልጽ የሚያሳይ ነው ብለዋል። ታሊባን ለዛሬው ጥቃት ሃላፊነት ወስዷል።

XS
SM
MD
LG