ዋሽንግተን ዲሲ —
አፍጋኒስታን ውስጥ አንድ ሞተር ቢስኪሊት የሚነዳ አጥፍቶ ጠፊ ባግራም የአየሮፕላን ማረፍያ አጠገብ በነበረ የዩናትድ ስቴትስ (United States) እና የፍጋኒስታን የጣምራ ጥበቃ ቦታ ላይ ባደረሰው ጥቃት 6 የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ሀገሮች ድርጅት ወታደሮች እንደተገደሉ ሶስት ደግሞ እንደቆሰሉ NATO አረጋግጧል።
ባግራም ወያደራዊ አየሮፕላን ማረፍያ አፍጋኒስታን ውስጥ ከሚገኙት ወታዳራዊው ሰፈሮች ትልቁ እንደሆነና በደረሰው ጥቃት ላይ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን የ (NATO) ቃል አቀባይ ማይክል ላውሆርን (Michael Lawhorn) ገልጸዋል። የዜና ዘገባ አለን ከድምጽ ፋይሉ ያዳምጡ።