በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕረዚዳንት ኦባማ የ US ወታደሮችን ከአፍጋኒስታን ማስወጣት እንደሚጀምሩ አስታወቁ


የ United States ፕረዚዳንት ባራክ ኦባማ ትላንት ከ White House ቤተ መንግስት ባደረጉት ንግግር 10,000 የሚሆኑ የ United States ወታደሮች እስከ ያዝነው አመት ማብቅያ ባለው ጊዜ ውስጥ ከአፍጋኒስታን እንደሚወጡ አስታውቀዋል። እስከ መጪው አመት ባለው ጊዜ ደግሞ ሌሎቹ ለማጠናከርያ የተላኩት 33,000 ወታደሮች ከሃገሪቱ እንደሚወጡ ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት አፍጋኒስታን ውስጥ 100,000 የሚሆኑ የ United States ወታደሮች፣ ወደ 10 አመታታ የሚጠጋ ዕድሜ በሆነው ጦርነት እየተዋጉ ነው።

ፕረዚዳንት ኦባማ ስለቀሩት የ United States ወታደሮች ሲያብራሩ "የአፍጋኒስታን የጸጥታ ሀይሎች የፋና ወጊነት ቦታ እየያዙ ሲሄዱ ቀስ በቀስ ወደ ሀገራቸው ይመለሳሉ” ብለዋል።

የአፍጋኒስታን ፕረዚዳንት ሐሚድ ካርዛይ በበኩላቸው በፕረዚዳንታዊ ቤተ-መንግስታቸው ሆነው ሲናገሩ፣ የ United States ወታደሮች መውጣት ዜናን በአዎንታዊ መንፈስ ተቀብለውታል። "አሁን የሀገሪቱን ጸጥታ የማስከበሩ ሃላፉነት መውሰዱ የአፍጋኒስታን ወጣቶች ፈንታ ነው" በማለት አስገንዝበዋል።

XS
SM
MD
LG