በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻርለስ ንጉሥ መሆናቸው በይፋ ታወጀ  


የእንግሊዝ ሳልሳዊ ንጉሥ ቻርለስን ንግስና ያወጀው ጉባኤ ለንደን በሚገኘው የቅዱስ ጄምስ ቤተ መንግሥት ባካሄደው ስብሰባ ላይ እአአ 2/10/2022
የእንግሊዝ ሳልሳዊ ንጉሥ ቻርለስን ንግስና ያወጀው ጉባኤ ለንደን በሚገኘው የቅዱስ ጄምስ ቤተ መንግሥት ባካሄደው ስብሰባ ላይ እአአ 2/10/2022

የዳግማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥ ህይወት ማለፉን ተከትሎ ልጃቸው ቻርልስ ዛሬ በለንደን ቅዱስ ጄምስ ቤተ መንግሥት በተካሄደ ሥርዓት ንግሥናቸውን ተቀብለዋል።

ንጉሡ ቻርለን እናታቸው ሐሙስ ዕለት ማረፋቸውን ተከትሎ ወዲያውኑ ንጉሥ የሆኑ ሲሆን ከዚህ በኋላ ሳልሳዊ ንጉሥ ቻርልስ በመባል ይጠራሉ።

ቅዳሜ ዕለት ንግሥናውን ባወጀው ጉባዔ የተካሄደው ሥነ ሥርዓት በቴሌቭዥን በቀጥታ የተላለፈው ለመጀመሪያ ግዜ ነው።

የ73 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ቻርለስ ንግሥና ለመቀበል በዕድሜ የገፉ የመጀመሪያው ንጉሥ ሲሆኑ እናታቸው በ96 ዓመታቸው ህይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ፣ ላለፉት ሰባት አስርት ዓመታት እንዳደረጉት፣

"በታማኝነት፣ በአክብሮት እና በፍቅር" እንደሚያገለግሉ ተናግረዋል።

ቻርልስ አርብ ዕለት ከባለቤታቸው ካሚላ ጋር በመሆን ስኮትላንድ ከሚገኘው ባልሞራል ካስል የተሰኘው መኖሪያ ቤታቸው ተነስተው ለንደን የሚገኘው ቤተ መንግሥት ሲደርሱ በርካቶች መልካም ምኞት ገልፀውላቸዋል።

አርብ ዕለት በቅዱስ ጳውሎስ ካቴድራል ለንግሥቷ ማስታወሻ በተካሄደ ሥነ ሥርዓት ላይ ወደ 2ሺህ የሚጠጉ ሰዎች መገኘታቸው ታውቋል። የዳግማዊ ንግሥት ኤልሳቤጥ የቀብር ሥነ ሥርዓት በመጪዎቹ ቀናት የሚካሄድ ሲሆን ሌሎች ንጉሣዊ ቤተሰቦች እና ክቡራን እንግዶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቀል።

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንም ለቀብሩ ወደ እንግሊዝ እንደሚጓዙ አስታውቀዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ አውስትራሊያኖች በንግሥት ኤልሳቤጥ ሞት በከፍተኛ ሁኔታ ማዘናቸው ተገልጿል። የሀገሪቱ የፖለቲካ አመራሮች ሀዘናቸውን ለመግለፅ ዛሬ በፌዴራል ፓርላማቸው ጉንጉን አበባ ያኖሩ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንተኒ አልባኒዝ "ንግሥቷ ለአውስትራኢያኖች ጎርፍ እና ሰደድ እሣት በመሳሰሉ አሳዛኝ አደጋዎች ውስጥ ሲያልፉ አሳይታ የነበረውን ርህራሄ አስታውሰዋል"

እአአ በ1954 አውስትራሊያን በመጎብኘት ንግሥት ኤልሳቤጥ የመጀመሪያዋ የእንግሊዝ ንጉሣዊ ቤተሰብ ሲሆኑ በወቅቱ ወደ 70 ከመቶ የሚገመት ህዝብ እሳቸውን ለማየት አደባባይ ወጥቶ ነበር።

XS
SM
MD
LG