በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእንግሊዟ ንግሥት ዳግማዊት ኤልዛቤጥ ጤንነት አሳስቧል


የእንግሊዟ ንግሥት ዳግማዊት ኤልዛቤጥ
የእንግሊዟ ንግሥት ዳግማዊት ኤልዛቤጥ

ሐኪሞች “ የግርማዊቷ ጤንነት ያሳሳባቸው በመሆኑ” የእንግሊዝ ንግሥት ዳግማዊት ኤልዛቤጥ የህክምና ክትትል ስር ናቸው ሲል ንግሥቲቱ የሚገኙበት ባኪንግሃም ቤተመንግሥት አስታወቀ፡፡

የንግሥቲቱ ቤተሰቦች ከ96 ዓመቷ ንግሥት ኤልሳቤጥ ጋር ለመሆን እሳቸው ወደሚገኙበት ስኮትላንድ ማቅናታቸውም ተነግሯል፡፡

የመታመማቸው ዜና የተነገረው ዶክተሮቹ ንግሥቲቱ ከአማካሪዎቻቸው ጋር በበይነ መረብ ላይ ያደርጉት የነበረውን ስብሰባ እንዲያቋረጡ ከነገሯቸው በኋላ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ባላፈው ማክሰኞ አዲስ የተመረጡት ሊዝ ትረስ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑ በይፋ በየጠቁበት ቀን ማግስትም ሙሉውን ቀን እረፍት እንዲያደርጉ በሀኪሞች ተነግሯቸው እንደነበርም ተነገሯል፡፡

XS
SM
MD
LG