በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዳግማዊት ኤልዛቤጥ አረፉ


ፎቶ ፋይል፦የእንግሊዝ ንግሥት ዳግማዊት ኤልዛቤጥ
ፎቶ ፋይል፦የእንግሊዝ ንግሥት ዳግማዊት ኤልዛቤጥ

የእንግሊዝ ንግሥት ዳግማዊት ኤልዛቤጥ በ96 ዓመታቸው ስኮትላንድ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ዛሬ ማረፋቸው ተዘግቧል።

የበኩር ልጃቸውና አልጋ ወራሽም ሆነው የቆዩት የዌልስ ልዑል ቻርልስ ንግሥናውን ተረክበዋል።

ዳግማዊት ኤልሳቤጥ ዙፋኑ ላይ ለ70 ዓመታት ለዘለቀ ጊዜ በመቆየታቸው ቁጥሩ እጅግ የበዛ የዩናይትድ ኪንግደም ዜጋ ከእርሳቸው ሌላ የሃገር መሪ አያውቅም።

ንግሥት ኤልሳቤጥ የንጉሣውያንን ቤተሰብና ሥርዓት በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ሁሉ ውስጥ በጥንካሬ የመሩ እንደነበርም ተነግሮላቸዋል።

በታሪክ ከማንም በላይ ቁጥራቸው የበዛ የዓለም ዕውቅ ሰዎችንና ታላላቅ መሪዎችን ያገኙ ገናና መሆናቸውም ተመስክሮላቸዋል።

ምስላቸው በቴምብሮች፣ በሣንቲሞችና በገንዘብ ኖቶች ላይ ተደጋግመው ከታተሙላቸው ታላላቅ ሰዎች መካከል ቀዳሚዋ እንደነበሩም ተዘግቧል።

ይሁን እንጂ “ውስጣቸውና የግል አመለካከትና ህይወታቸው ለብዙዎች እንቆቅልሽ እንደሆነ ቀርቷል” ሲል አሶሲየትድ ፕሬስ ዘግቧል።

ዳግማዊት ኤልዛቤጥ ከዩናይትድ ኪንግደም ሌላ ከሰላሣ በላይ ለሚሆኑ የጋራ ብልፅግናው አባል የሆኑ የአውሮፓ፣ የእስያና የአሜሪካ ሉዓላዊ ሃገሮችም በንግሥትነታቸው ርዕሰ ብሄር እንደነበሩ ይታወቃል።

XS
SM
MD
LG