በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፎርት መክመሪውን ሰደድ እሳት መቆጣጠር አልተቻለም


በካናዳ አልበርታ ግዛት ፎርት መክመሪ የተነሳው ሰደድ እሳት
በካናዳ አልበርታ ግዛት ፎርት መክመሪ የተነሳው ሰደድ እሳት

እስካሁን ሺሕ ስድስት መቶ ሕንፃዎች ወድመዋል። ነዋሪዎች መጠለያ ውስጥ ገብተዋል። እስከ ዐሥራ አምስት ሺሕ የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን ይኖሩበታል በሚባለው በካናዳ አልበርታ ግዛት ፎርት መክመሪ ከተማ የተነሳውን ሰደድ እሳት መቆጣጠር ስላልተቻል ነዋሪዎች ከተማዋን ለቀው ውጥተው በመጠለያዎች ገብተዋል። ጽዮን ግርማ የአካባቢው ነዋሪን አቶ ሰይፈ መኮንን አነጋግራ ተከታዩን ዘግባለች።

የካናዳይቱ አልበርታ ግዛት ውስጥ የፎርት መክመሪ ከተማ ነዋሪዎች ሙሉ በሙሉ ከተማይቱን ለቀው እንዲወጡ ትናንት ታዘዋል። ዘጠና ሺሕ የሚሆኑት የፎርት ማክመሪ ነዋሪዎች እንዲወጡ የታዘዙት አካባቢውን እያጋየ ያለውን ሰደድ እሳት ማቆም ወይም መቆጣጠር ባለመቻሉ እንደሆነ ተገልጿል።

በእሳቱ ምክንያት በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት እስካሁን እንደሌለ ታውቋል። በዚህ አካባቢ አስራ አምስት ሺሕ የሚደርስ ኢትዮጵያውያን ይኖራሉ ተብሎ የሚገመት ሲሆን በዚህ አካባቢ የሚኖረውና በኢትዮጵያ ጋዜጠኛ የነበረው ሰይፈ መኮንን እሳቱ ዛሬም እንደቀጠለ ነው ይላል።

ሰደዱን ለማስቆም እየተረባረቡ ካሉት ባለሥልጣናት አንዱ የሆኑት ቻድ ሞሪሰን የእሳቱ መንስኤ መብረቅ ይሁን ወይም ሰው የጫረው ገና እንደማያውቁና እያጣሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያድምጡ።

የፎርት መክመሪውን ሰደድ እሳት መቋቋም አልተቻለም
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:11 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG