በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የካናዳ ሰደድ እሳት 100 ሺሕ ሰው አፈናቀለ


ሰደድ እሳት በካናዳ
ሰደድ እሳት በካናዳ

እስከ ከዐሥር እስከ 15 ሺሕ የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን ይኖሩበት የነበረ አካባቢ ነው ተብሏል። ቤት ንብረታቸው እየወደመ ነው።

በካናዳ በነዳጅ ሃብቷ በምትታወቀው አልበርታ ፎርት መክመሪ በተባለ ከተማ የተነሳውን ሰደድ እሳት የሸሹ 100 ሺህ ሰዎች አካባቢውን ለቀው እየወጡ ነው።

በሰደድ እሳቱ ከተማዋ ሙሉ ለሙሉ እየወደመች መሆኑ እየተነገረ ነው። እስካሁን በሰው ሕይወት ላይ ግን የደረሰ አደጋ የለም።

ሰደድ እሳት በካናዳ
ሰደድ እሳት በካናዳ

የከተማው አስተዳዳሪዎች ትኩረታችን ሰውን ማትረፍ በመሆኑ ሰው ከተማውን ለቆ እንዲወጣ እያደረግን ነው ብለዋል። በዚህ አካባቢ በርካታ ኢትዮጵያውያን እንደሚኖሩበት ይነገራል። በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ጽዮን ግርማ አቶ ሰይፈ መኮንን ወደተባለ የአካባቢው ነዋሪ ማምሻውን ደውላ ተከታዩን ዘገባ አጠናክራለች።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያድምጡ።

የካናዳ ሰደድ እሳት 100 ሺሕ ሰው አፈናቀለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:38 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG