በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቡሩንዲ ሰላም አስከባሪ ጦር “አትቀበልም”


የቡሩንዲ መንግሥት የአፍሪካ ኅብረትን ሰላም አስከባሪ ጦር እንደማይቀበል በይፋ አስታውቋል፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:03:40 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የቡሩንዲ መንግሥት የአፍሪካ ኅብረትን ሰላም አስከባሪ ጦር እንደማይቀበል በይፋ አስታውቋል፡፡

የቡጁምቡራ ምክንያት ኅብረቱ ውሣኔው ላይ ከመድረሱ በፊት አላማከረንም የሚል እንደሆነ ታውቋል፡፡

የቡሩንዲ ፓርላማ ከትናንት በስተያ - ሰኞ ተሰብስቦ ባሣለፈው ዋሣኔ የአፍሪካ ኅብረት ሠራዊት ቢልክ እንደ “ወራሪ ኃይል” እንደሚታይ አስጠንቅቋል፡፡

የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ፒየር ንኩሩንዚዛና የካቢኔው ሚኒስትሮች ሁሉ የሚገኙበት የቡሩንዲ ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት የፓርላማውን ውሣኔ ተከትሎ የሰላም አስከባሪ ኃይልን መላክ ሃሣብ ውድቅ አድርጓል፡፡

“እኛን ሳታማክሩ ያሣለፋችሁት ውሣኔ የዲፕሎማሲን በጎ ተግባር የሚፃረር ነው” ብለውታል የሃገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አለን ኛሚትዋ፡፡

በሌላ በኩል ግን የአፍሪካ ኅብረት የሰላምና የደኅንነት ምክር ቤት ባለፈው ዓርብ ውሣኔውን ሲያሣልፍ የቡጁምቡራም ሃሣብ የተሰማና ግምት ውስጥ የገባ እንደነበር የኅብረቱ ኮሚሺን ምክትል ሊቀመንበር ኤራስቱስ ምዌንቻ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG