በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ ኅብረት ጦር ቡሩንዲ ለመላክ ወሰነ


ቡሩንዲ ውስጥ አሕጉራዊ አቃቤ ሰላም ኃይል እንዲሠማራ የአፍሪካ ኅብረት የሰላምና የፀጥታ ምክር ቤት ከትናንት በስተያ ቅዳሜ ወስኗል።

ቡሩንዲ ውስጥ የዘር ፍጅት አዝማሚያ ሲጠነሰስ ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ እጁን አጣጥፎ አይመለከትም ሲሉ የአፍሪካ ኅብረት ምክትል ሊቀመንበር ኤራስቱስ ሞኤንቻ አስገንዝበዋል።

የአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ኃይሉን ለማሠማራት የወሰነው አመፅን ለማቆምና ሲቪሎችን ከአደጋ ለመጠበቅ መሆኑን ምክትል ሊቀመንበሩ ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ መንግሥታቸው የኅብረቱን ሰላም አስከባሪ ኃይል የሚያየው “እንደወራሪ ጦር” መሆኑንና የምክር ቤቱን ውሣኔ እንደሚቃወም የፕሬዚዳንቱ ምክትል ቃል አቀባይ ዣን ክሎድ ካሬርዋ ለፈረንሣዩ የዜና ወኪል ትናንት /ዕሁድ/ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የአፍሪካ ኅብረት ጦር ቡሩንዲ ለመላክ ወሰነ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:37 0:00

አስተያየቶችን ይዩ (2)

XS
SM
MD
LG