ቡርኪና ፋሶ የቀድሞ ፕረዚዳንት ብሌይስ ኮምፓኦሬ (Blaise Compaore) አጋር የነበሩትና በኋላ ተቃዋሚያቸው የሆኑትን ሳሊፍ ዲያሎን (Salif Diallo) የብሄራዊ ሸንጎ ሊቀመንበሩዋ አድርጋ መርጣለች።
እንደሳቸው የኮምፓኦሬ አጋር በበሁዋላ ተቃዋሚ የሆኑት ማርክ ክሪስቲያን ካቦሬ ፕረዚዳንት ሆነው ቃለ መሃላ ትናንት የፈጸሙ ሲሆን ዲያሎም ወዲያው ስልጣናንቸውን ተረክበዋል።
ዲሎና ካቦሬ ከቀድሞው ፕረዚዳንት ተቆራርጠው የራሳቸውን ፓርቲ ከሁለት ዓመት በፊት አቋቁመዋል።
ኮምፓኦሬ ለሃያ ሰባት ዓመታት በቆዩበት መንበረ ስልጣን ለመቆየት በመዳዳታቸው ምክንያት በተፈጠረ ህዝባዊ ዓመጽ ነው ከስልጣን የተባረሩት። የዜና ዘገባውን ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።