ዋሽንግተን ዲሲ —
የቀውድሞ የቡርኪና ፋሶ ጠቅላይ ሚኒስትር ሮች ማርክ ክርስትያን ካቦሬ (Roche Marc Christian Kabore) የሀገሪቱን ፕረዚዳንታዊ ምርጫ አሸነፉ።
በጉልበተኛው መሪ ብሌዝ ካምፓኦሬ ስር የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት Kabore ከአምሳ ከመቶ በላይ ድምጽ እንዳገኙ የምርጫ ባለስልጣኖች ትላንት ማታ አስታውቀዋል።
ተመራጩ ፕረዚዳንት ውጤቱ ይፋ እንደተደረገ ባሰሙት ንግግር ወዳያውኑ ስራ ለመጀመር ቃል ገብተዋል። ደጋፊዎቻቸው በመንገዶች ላይ ባንዴራ ሲያውለበልቡና የመኪና ጥሩምባ ሲያሰሙ በቴሌቪዥን ታይተዋል።
ዋናው የተመራጩ ፕረዚዳንት ተወዳዳሪ Zephirin Diabre ከ 30 ከመቶ ድምጽ በታች ነው ያገኙት። Diabre የምርጫው ውጤት እንደተሰማ Kaboreን እንኩኣን ደስ ያሎት እንዳልዋቸው የፈረንሳይ የዜና አገልግሎት ከመዲናይቱ ዋጋዱጉ ባስተላለፈው ዘገብ ገልጿል።
ቡርኪና ፋሶ እአአ በ 1960 አም ነጻ ከወጣችበት ጊዚ አንስቶ በአብዛኛው በጉልበት ስልጣን በያዙ አምባገነኖች ትምራ እምደነበር ይታወቃል። የዜና ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።