በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናትድ ስቴትስ የቡርኪና ፋሶን ምርጫ "ሰላማዊና ስነ-ስርአት የተመላበት” ነው ብላለች


የቀውድሞ የቡርኪና ፋሶ ጠቅላይ ሚኒስትር ሮች ማርክ ክርስትያን ካቦሬ (Roche Marc Christian Kabore)
የቀውድሞ የቡርኪና ፋሶ ጠቅላይ ሚኒስትር ሮች ማርክ ክርስትያን ካቦሬ (Roche Marc Christian Kabore)

ዩናትድ ስቴትስ (United States) የቡርኪና ፋሶ ህዝብና መንግስት የሀገሪቱን አንድነት ለመጠበቅና የሀገሪቱን ተቋማት ለማጠናከር በሚያደርጉት ጥረት ከነሱ ጋር በአጋርነት መስራቱን ለመቀጠል በጉጉት እንደምትጠብቅ በመግለጫ አስታወቀች።

ዩናትድ ስቴትስ (United States) ቡርኪና ፋሶን ባለፈው እሁድ "ሰላማዊና ስነ-ስርአት የተመላበት ምርጫ” በማካሄድዋ እንኳን ደስ ያለሽ ብላታለች። በምርጫው የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሮች ማርክ ክርስትያን ካቦሬ (Roche Marc Christian Kabore)እንደተመረጡ የሚታወቅ ነው።

የዋይት ሃውሱ መግለጫ የቡርኪና ፋሶ ህዝብ “የዲሞክራሲን መርሕ ለመጠበቅ ላሳየው ቁርጠኛነት” አሞግሶታል። የቡርኪና ፋሶ ህዝብና መንግስት የሀገሪቱን አንድነት ለመጠበቅና የሀገሪቱን ተቋማት ለማጠናከር በሚያደርጉት ጥረት ዩናትድ ስቴትስ (United States)ከነሱ ጋር በአጋርነት መስራቱን ለመቀጠል በጉጉት ትጠብቃለች ሲልም መግለጫው አክሎበታል።

ተመራጩ ፕረዚዳንት ካቦሬ (Kabore) በበኩላቸው ትላንት ለማሸነፍ በመቻላቸው ደጋፊዎቻቸውን አሞግሰው ወድያኑ ስራ ለመጀመር ቃል ገብተዋል። ያገኙትን ድል ባለፈው አመት የረዥም ጊዜ የሀገሪቱ ፕረዚዳንት የነበሩትን ብሌዝ ካምፓኦሬን ከስልጣን ለማወረድ በተደረገው ህዝባዊ መነሳሳት ህይወታቸን ለሰጡት መታሰብያ ይሁን ብለዋል።

ቀድሞ የካምፓኦሬ ተባባሪ የነበሩት ካቦሬ (Kabore)የትናቱን ምርጫ ያሸነፉት ከ 53 ከመቶ በላይ ድምጽ በማግኘት ነው። የድምጽ ፋይሉን ለመስማት የድምጽ ፋይሉን ያዳምጡ።

ዩናትድ ስቴትስ የቡርኪና ፋሶን ምርጫ "ሰላማዊና ስነ-ስርአት የተመላበት” ነው ብላለች
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:19 0:00

XS
SM
MD
LG