በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጥቁር ሕዝቦች የመብት ትግል በአሜሪካ


የአፍሪካ አሜሪካዊያን የሲቪል መብት ንቅናቄ መሪ ማርቲን ሉተር ኪንግ ከአምስት አስርት ዓመታት በፊት “ህልም አለኝ” ንግግር መልእክቶች ዛሬ በከፊል ተሳክተው፤ የተቀሩት ደግሞ ለአሁኑ ወጣት አሜሪካዊ ትውልድ አንደ አርዓያና፤ ግብ ለመምታት መነሳሻ ሆኗል።

በእርግጥ አለማችን አንድ እየሆነች በመምጣቷ አሜሪካዊያን ወጣቶችና አዳጊዎች ዛሬ የሚጋፈጧቸው ፈተናዎችና ችግሮች ለኢትዮጵያና አፍሪካ እንዲሁም ሌሎችም ወጣቶች ፍጹም ልዩ በሆነ ኑራቸው፤ አንድነትን ሊያገኙበት የሚችሉበትም ነው።

ወጣት አሜሪካዊያን ስለ ዶር ኪንግና የመብት ትግሉ

“አንድ በጣም የሳበኝ ጉዳይ አፍሪካ አሜሪካዊያንን ለመርዳት ሲሰራ ሁሉንም ነው አብሮ ያቀፈው፣ በአብሮነት ያገናኘው። አሁን እኮ ሁሉም ሰው ተስማምቶ ይኖራል፤ እጅም ይጨባበጣል” ናይላ ባንክስ 12 ዓመት

“በርካታ ጊዜ አስረውታል። ብዙ ሰው ተስፋ ለመቁረጥ መታሰር ይበቃዋል። እሱ ግን ቀጠለ፤ ያሰበውን እስኪያሳካ ድረስ አላቆመም።” ጆናታን ዊሊያምስ 14 ዓመት; በጣም የሚገርምና አሪፍ ሰው ነው። ሁሉንም ነገር በሰላም ነው ያከናወነው፤ ያለምንም አይነት ሁከት። ለኔ እንዲህ ያለ መሪ በጣም ይስበኛል አርዓያም ይሆነኛል። የሊንዳ ማርቲኔዝ 14 ዓመት። “ሰዎች እርስበርስ የሚተያዩበት መንገድ አሁንም የተለያየ ነው። ማለቴ የቆዳ ቀለማቸውን አስቀድመው ያያሉ፤ ይሄ ለኔ መቅረት ያለበት ነገር ነው።”

“ብዙ የዘር ንግግሮች አሉ። ለምሳሌ ኢስያዊያን መንዳት አይችሉም ምናምን የሚሉ። ይሄ በጣም ደስ የማይል ነገር ነው። በዚህ ዘመን እንዲህ ያለ ንግግር ይሰማል። ጋር ነው የሚያጋባኝ ምክንያቱም ዛሬ ብዙ ሰው ተከባብሮ ነው የሚኖረው።” ጁሊያ ሊንክ

የጥቁር ሕዝቦች የመብት ትግል በአሜሪካ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:53 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

አሜሪካዊያን የሲቭል መብት መሪዎች ስለትግሉ

“ብዙ ወጣቶች ይሄንን ታሪክ እንደተሰጣቸው ቆጥርው ችላ እንዲሉት እንፈልጋለን። ለዚህም ምክንያት አለው። እኛ በ1963 ዓ.ም. ይሰማን የነበረው አይነት መድሎና በደል ለአሁኑ ትውልድ እንዳይተላለፍ ስለሆነ የታገልንው። እነዚህን መብቶች ሲኖሩባቸው እንጂ ሲታገሉላቸው ማየት የቀደምንውን አያስደስተንም።” የሲቪል መብት ተሟጋቿና በኮንግረስ የዋሽንግተን ዲሲ ወኪል ኤለኖር ሆልምስ ኖርተን

“ለነጭ ወንዶች፣ ለጥቁር ወንዶች፣ ለነጭ ሴቶች፣ ለጥቁር ሴቶች … ማብቂያ የሌላቸውን ልዩነቶች አጥብቄ እጠላ ነበር።” ኮንግረስማን ጆን ሉዊስ

“በመንገድ ላይ እንኳን አንድ ነጭ ሰው ከፊት ለፊት ከመጣ፤ መንገድ መልቀቅ አለብህ። ይሄ ብቻ አይደለም እስኪያልፉ ድረስ ማጎብደድም ይጠበቅብሻል። ይሄን ያላደረገ ሰው፤ ክብር አሳጣሃኝ ተብሎ የደበደባል ወይንም ይታሰራል።” የሲቪል መብት ታጋት ሆሊስ ውትኪንስ

የጥቁር ሕዝቦች የመብት ትግል በአሜሪካ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:40 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG