ዋሽንግተን ዲሲ —
የኢትዮጵያ መንግሥት፣ ከጥቂት ወራት በፊት በታሰሩት በኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ-መንበር በቀለ ገርባና በሌሎችም ላይ የመሠረተው የሽብርተኛነት ክስ፣ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥትን በፅኑ እንዳሳሰበው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል-አቀባይ ጃን ኪርቢ ቢሮ ይፋ የሆነው መግለጫ አመልክቷል።
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰኔ 12, 2003 ዓ.ም በኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ስለታሰረው ውብሸት ታየም መግለጫ አውጥቷል።
አዲሱ አበበ የመግለጫውን ይዘት ባጭሩ አቅርቦ በካሊፎርኒያ ስቴትስ ዩኒቨርሲቲ - ሳንበርናርዲኖ የህግና የፖለቲካ ሳይንስ ፕሮፌሰር ከሆኑት ከዓለማየሁ ገብረማርያም ጋር ወደ ያካሄደው ውይይት ይወስደናል።