በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በእሥላማዊ መንግሥት ላይ የሚወሰደው እርምጃ መዳከሙ ተነገረ


ቱኒዝያ ከሊብያ ጋር ያላትን ወሰን መዝጋቷ ሁለቱ የሊብያ ተገዳዳሪ መንግሥታት ወደ ውኅደት እንዲገቡ ግፊቱን እንደሚያበዛባቸው እየተሰማ ነው፡፡

ቱኒዝያ ከሊብያ ጋር ያላትን ወሰን መዝጋቷ ሁለቱ የሊብያ ተገዳዳሪ መንግሥታት ወደ ውኅደት እንዲገቡ ግፊቱን እንደሚያበዛባቸው እየተሰማ ነው፡፡

ቱኒዝያ ድንበሯን የዘጋችው ወሰኑ ላይ በምትገኝ ከተማ ውስጥ በተፈጠረ ግጭት 55 ሰው ከተገደለ በኋላ ነው፡፡

ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ ወገን ባይኖርም ከሁከቱ ባህርይ መረዳት እንደተቻለው እሥላማዊ መንግሥት ቡድን አካባቢውን ለመቆጣጠርና ይዞታውን ለማስፋት የሚያካሂደው ዘመቻ አካል ሳይሆን እንደማይቀር ተገምቷል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ሊብያ ውስጥ የእሥላማዊ መንግሥት ቡድንን ቀጣይ መንሠራፋት ማቆም የሚችል አፋጣኝ እርምጃ በፅንፈኛ ታጣቂዎቹ ላይ እንዲወሰድ ጥሪዎች እየተሰሙ ነው፡፡

ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ እሥላማዊ መንግሥት ላይ የሚወስዳቸው እርምጃዎች እየተዳከሙ መምጣት ቡድኑ ይዞታዎቹን ከሦሪያ፣ ከኢራቅና ከሊብያ ውጭም እያሰፋ እንዲሄድ ሰፊ ዕድል የከፈቱለት መሆኑን ቤይሩት የሚገኘው የአሜሪካ ጥናቶች ማዕከል ዳይሬክተር ካሜል ዋዝኔ አመልክተዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

በእሥላማዊ መንግሥት ላይ የሚወሰደው እርምጃ መዳከሙ ተነገረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:18 0:00

XS
SM
MD
LG