በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአምነስቲ ሪፖርት - የኢዮጵያና ኤርትራ መንግሥታት ምላሽ


ከአምነስቲ ኢንተርናሽናል የተገኘ ምስል
ከአምነስቲ ኢንተርናሽናል የተገኘ ምስል

የኤርትራ ወታደሮች ልክ የዛሬ ሦስት ወር በመቶዎች የሚቆጠሩ ሲቪሎችን በአክሱም ከተማ ጨፍጭፈው መግደላቸውን ፤ ይህም በሰብዓዊ ፍጡር ላይ እንደተፈፀመ ወንጀል የሚቆጠር መሆኑንዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል አዲስ ባወጣው ሪፖርት አመለከተ።

ከኅዳር 10 እስከ 21 ባሉት ቀናት ውስጥ በአክሱም ከተማና ነዋሪዎቿ ላይ የቦንብ ድብደባ፣ የጅምላ ግድያ፣አካል ጉዳት እና ዘረፋን ጨምሮ ከባድ የመብት ጥሰቶች መፈፀማቸውን ገልጿል። በተለይ ከኅዳር 19 እና20/ 2013 ዓ.ም ከ200 ሰዎች በላይ በጅምላ መገደላቸውንድርጅቱ የእማኞቹን ቃል ጠቅሶ ይፋ አድርጓል።

የኤርትራ መንግሥት አምነስቲ ያወጣው ሪፖርት ተገቢ ያልሆነ ክስ፣ እጅግ የሚያስቆጣና የማይቀበለው መሆኑን አስታውቋል። የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ ለሰብዓዊ መብት መከበር ትልቅ ትኩረት እንደሚሰጥ ገልፆ በጉዳዩ ላይ የተሟላ መረጃ ለማግኘት ግን ከብታው ላይ ከተሰበሰቡ መረጃዎች ማጣራትን እንደሚጠይቅ አስታውቋል።

አምነስቲ ያወጣውን ሪፖርት በተመለከተ የድርጅቱን የአፍሪካ ቀንድ አጥኒ አቶ ፍሰሃ ተክሌን እና የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤታ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲን ያነጋገረችው ጽዮን ግርማ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራለች።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

የአምነስቲ ሪፖርት - የኢዮጵያና ኤርትራ መንግሥታት ምላሽ
please wait

No media source currently available

0:00 0:22:31 0:00


XS
SM
MD
LG