በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቃለ ምልልስ ከአምነስቲ ኢንተርናሽናል አጥኒ ጋር


በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ "ጋዋ ጋንቃ" ተብሎ በሚጠራው ቀበሌ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ 54 የአማራ ብሔር ተወላጆች በአንድ ትምሕርት ቤት ውስጥ በታጣቂዎች መገደላቸውን ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲኢንተርናሽናል ትላንት ባወጣው መግለጫ አስታወቀ። ይህ ቁጥር እስካሁን የተቆጠረውን አስክሬን መሰረት ያደረገ እንደሆነ ጠቅሶ ቁጥሩ ሊጨምር ይችላል ብሏል።

ከዚህ ቀደም በአካባቢው ላይ በነበረ የፀጥታ አለመረጋጋት ምክኒያት ፀጥታውን ለመጠበቅ በቦታው የነበረው የመከላከያ ሰራዊት ቅዳሜ ዕለት ቦታውን ለቆ መውጣቱን እናጥ ቃቱን ፅሞታል በሚል የሚጠረጠርው የኦሮሞ ነፃነት ጦር ቦታውን መቆጣጠሩን የገለፀው አምነስቲ፤ እሁድ ለት ሕፃናት፣ እናቶችን እና ዛውንቶችን ለስብሰባ ትፈለጋላችሁ በሚል በአንድ ትምሕርት ቤት ውስጥ ካስገቧቸው በኋላ ድምፅ ባላቸው መሳሪያዎች እንደጨረሷቸው እማኞቼ ናቸው ያላቸውን ከጥቃት የተረፉ ሟች ቤተሰቦቹን ጠቅሶ በመግለጫው ይፋ አድርጓል።

አባቱ እህቱና የባለቤቱ አያት በዚህ ጥቃት የተገደሉበትን እማኝ ማነጋገሩን የገለፀው አምነስቲ ወንድሙን የወንድሙን ባለቤትእና ሦስት ልጆቻቸውን በአንድ ላይ ያጣ ሌላ ተጎጂም ማነጋገሩን በመግለጫው አትቷል። የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግልጫ የሟቾች ቁጥር 32 ብለዋል።

ጽዮን ግርማ በአምነስቲ ኢንተርናሽናል በአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብቶች ጉዳዮች አጥኒ የሆኑትን አቶፍሰኃ ተክሌን በመግለጫው ዙሪያ አነጋግራቸዋለች ቀጥሎ ይቀርባል።

ቃለ ምልልስ ከአምነስቲ ኢንተርናሽናል አጥኒ ጋር
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:55 0:00


XS
SM
MD
LG