በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰሜን ኢትዮጵያን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለማስቀጠል ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ


የሰሜን ኢትዮጵያን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለማስቀጠል ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:42 0:00

የሰሜን ኢትዮጵያን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለማስቀጠል ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ

በአማራ አፋር እና ከፊል ትግራይ ክልሎች የተቋረጠውን ኤሌትሪክ ኃይል ለማስጀመር እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ። አገልግሎቱ የተቋረጠው በኤሌክትሪክ ኀይል መሥመሮች ላይ ደረሰ የጦር መሳሪያ ጥቃት መሆኑን የአማራ ክልል ፖሊስ እና ኤሌትሪክ ኃይል ገልፀዋል። በጥቃት አድራሾቹ ማንነት ላይ መንግሥትና የፋኖ ታጣቂዎች እየተወነጃጀሉ ነው። የዘገባውን ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ተጨማሪ መረጃ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ማምሻውን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ ጉዳት ደርሶበት የተበጠሰው የባህር ዳር - ደብረታቦር - ንፋስ መውጫ - ጋሸና - አላማጣ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተጠግኖ አገልግሎት መስጠቱን አስታውቋል።

ጥገናውን ተከትሎ ባህርዳር፣ ጎንደር እና የትግራይ ከተሞች የኤሌክትሪክ ኀይል ስርጭት ማግኘታቸውን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሰሜን ምዕራብ ሪጅን የኦፕሬሽንና ጥገና መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ውበት አቤ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

ወልዲያ፣ ኮምቦልቻና በአካባቢው ያሉ ከተሞች እንዲሁም በኮምቦልቻ በኩል ኃይል ሲያገኙ የነበሩትን ሠመራ እና ሌሎች ከተሞችን ለማገናኘት ጥረቱ መቀጠሉን አብራርቷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG