በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አክሱም እና ዓድዋ የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘት ጀመሩ


የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ መላኩ ታዬ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ መላኩ ታዬ

አክሱም እና ዓድዋ ከተሞች ከትናንት ምሽት ጀምሮ የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘታቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

የተቋሙ ኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ መላኩ ታዬ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ ሰሞኑን ከሽረ ከተማ በተዘረጋ ባለ 66 ኪሎ ቮልት የማስተላለፊያ መስመር የአክሱም፣ የዓድዋ እና የውቕሮ ማራይ ከተሞች የሀይል ተጠቃሚዎች ሆነዋል፡፡

በሰሜኑ ጦርነት በርካታ ከተሞች ለረዥም ጊዜ የኃይል አገልግሎት ተቋርጦባቸው እንደቆዩ የገለፁት አቶ መላኩ "የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ ጉዳት የደረሰባቸውን የማስተላለፊያ መስመሮች በመጠገን፣ የትግራይ ከተሞችን የኃይል ተጠቃሚዎች ለማድረግ እየተሠራ ነው" ብለዋል፡፡

ዳይሬክተሩ ከተወሰኑ ቀናት በፊት የመቐለ እና ሽረ ከተሞችን ጨምሮ የተወሰኑ የትግራይ ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘታቸውን አስታውሰዋል፡፡

“ሌሎች የትግራይ ከተሞችም ተመሳሳይ በሆነ አጭር ጊዜ ውስጥ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ይሆናሉ” ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ለህዝቡ ኃይል ባለማቅረቡ ካጣው ገቢ በተጨማሪ፣ በመሰረተ ልማት ላይ 2.8 ቢሊዮን ብር የሚገመት ውድመት መድረሱን አቶ መላኩ አመልክተዋል፡፡

“የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ይህን ሁሉ ተቋቁሞ ለህብረተሰቡ ኃይል ለማቅረብ እየሰራና በተለያዩ አቅጣጫዎችም የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ጥገናን እያከናወነ መሆኑን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡

XS
SM
MD
LG