በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ የዕድገትና የተጠቃሚነት ዕድል ድንጋጌ


የአፍሪካ የዕድገትና የተጠቃሚነት ዕድል ድንጋጌ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:01 0:00

የአፍሪካ የዕድገትና የተጠቃሚነት ዕድል ድንጋጌ

ዩናይትድ ስቴትስ ኢትዮጵያን ከአጎአ እድል ተጠቃሚነት በመሰረዟ ቅሬታ እንደተሰማው የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ።

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ትናንት ማክሰኞ እለት ለሀገራቸው ኮንግረስ በጻፉት ደብዳቤ "ዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ፈፅማለች" በሚል ነው ኢትዮጵያን ከአጎአ እድል ተጠቃሚነት ለማገድ ማቀዳቸውን የገለጹት።

የፕሬዚደንቱን ውሳኔ በመቃወም የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ውሳኔ ምክንያታዊ እንዳልሆነ ጠቅሶ ሀገሪቱ ውሳኔዋን እንድትቀይር አሳስቧል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናትና ሌሎችም የሚመለከታቸው አካላት፣ ውሳኔው ከመተላለፉም በፊት ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ የቆዩ ሲሆን ከነዚህም አንዱ የሆነው፣ የአሜሪካ ኢትዮጵያዊያን የህዝብ ጉዳይ ኮሚቴ የተባለ ተቋም ሊቀመንበር አቶ መስፍን ተገኔ፣ ባይደን የደረሱበት ውሳኔ ተገቢ እንዳልሆነ ጠቅሰው ይሞገታሉ።

XS
SM
MD
LG